( ትምህርት አንድ ) የትምህርት ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ……… ዘፍጥረት 17 ፥ 4 _...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ………. ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ የተወደዳችሁ ወገኖች በቅድሚያ የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ በማለት ዛሬ በአዲስ የትምህርት ርዕስ ወደ እናንተ መጥቻለሁ የትምህርቱም ርዕስ እንዲህ የሚል ነው ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ………. ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ በማለት ይናገራል መጽሐፍቅዱሳችን ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ለብዙዎች እንደሚነገር ለዘሮቹም አይልም ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ ይለናል ገላትያ 3 ፥ 16 ታድያ ይህንን ሃሳብ ከዘፍጥረት 17 ፥ 4 _ 8 ከተጻፈው ሃሳብ ጋር በማመሳከር በሰፊው ልንመለከተው እንችላለን ይሁን እንጂ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም ይለናል ገላትያ 3 ፥ 17 ይህ ምን ማለት ነው ስንል ሕግ የመጣው እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቤት አራት መቶ ሠላሳ ዓመቱ ተፈጽሞ በተስፋው ቃል አማካኝነት ተጎብኝተው ከወጡ በኋላ ነው በዘፍጥረት 15 ፥ 12 _ 16 ፣ የሐዋርያት ሥራ 7 ፥ 6 _ 8 በተጻፈው ሃሳብ በአብርሃም በኩል ለእስራኤል የተነገረውን ተስፋ እና ጉብኝቱንም ጭምር እናይበታለን ታድያ የብሉይ ኪዳኑ እስራኤል ከባርነት ቤት ተጎብኝቶ ሲወጣ በተስፋው ቃል ነው እንጂ የወጣው በሕጉ አይደለም ሕጉ በሙሴ በኩል እስራኤል ከባርነት ቤት ከውጡ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የመጣ ነውና እስራኤል ከባርነት ቤት ሊወጡ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን እስኪሽር ድረስ አያፈርስም የሚሽርና የሚያፈርስም አይደለም ይህ ማለት ደግሞ እስራኤል ከባርነት ቤት የወጡት በተስፋው ቃል ነው እንጂ በሕጉ አይደለም ማለትን የሚያሳይ ነው ሙሴም አጥፊው የበኩሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደም መርጨትን በእምነት ካደረገ በኋላ በግብጻውያን በማንኛውም ቤቶች ሞተ በኩር መጣ ለዚህም ነው እንግዲህ ፈርኦንም ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ ከሕዝቤ መካከል ውጡ ሂዱም እንዳላችሁም እግዚአብሔርን አገልግሉ እንዳላችሁም መንጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ውሰዱ ሂዱ እኔንም ደግሞ ባርኩኝ ያላቸው ዘጸአት 12 ፥ 24 _ 32 ፤ ዕብራውያን 11 ፥ 28 ከዚህም ሌላ ሙሉውን ሃሳብ ለማግኘት ዘጸአት 12 ን በሙሉ ማንበብ መልካም ነው ስለዚህ የብሉይ ኪዳኑ እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቤት የወጡት ሕጉ ከመምጣቱ በፊት በነበረውና ለአብርሃምም በተነገረው የተስፋ ቃል ነው ሌላው በተስፋው ቃል ለመውጣታቸው የፈርኦን የራሱ ንግግር በቂ ማስረጃ ነው እንዳላችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ ሂዱ ብሎአልና እስራኤል በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል አስቀድመው የተባሉ ስለሆኑ የግብጽ ንጉስ ፈርኦንም እንዳላችሁም ሂዱ እግዚአብሔርንም አገልግሉ እኔንም ባርኩኝ አላቸው ሌላው ትልቁና ለእኛም አስደናቂ የሆነው ይህ የተስፋ ቃል አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳን ያለበት የተስፋ ቃል ስለሆነ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ወይንም የመጣው ሕግ የማይሽረውና የማያፈርሰው መሆኑ ነው በመሆኑም በብሉይ ከዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ሰዎች ከባርነት ቤት የሚፈቱትና ነጻ የሚወጡት አስቀድሞ በተረጋገጠው ኪዳንና የተስፋ ቃል ነው ታድያ ይህንኑ የተስፋ ቃል ነው ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ለብዙዎች እንደሚነገር ለዘሮቹም አይልም ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ በማለት ሐዋርያው የነገረን በመሆኑም በዚህ አስቀድሞ በእግዚአብሔር በተረጋገጠው ኪዳንና የተስፋ ቃላችን በሆነው በክርስቶስ ዛሬ ላይ በሐዲስ ኪዳን ያለን ሕዝቦች ከባርነት ቤትና ከሰይጣን እስራት ከጨለማውም ግዛት በዚሁ በክርስቶስ ለአንዴና ለዘላለም ተፈተናል ከዚሁ ባርነትም ተላቀናል ፣ ወጥተናል የብሉይ ኪዳን እስራኤል ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ ነው ከግብጽ የባርነት ቤት በሕጉ ሳይሆን በዚሁ የተስፋ ቃል የወጡት አጥፊው የበኩሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨት ያደረገላቸው ሙሴ ነው ለእኛ በሐዲስ ኪዳን ላይ ላለን ሕዝቦች ግን ፋሲካችን የሆነና ደሙንም በእኛ ላይ በመርጨት ከባርነት ቤት ከሰይጣንም ግዞት ለዘላለም ያወጣን ክርስቶስ ነው ለዚህም ነው ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾ አይደለም ሲል ሐዋርያው የነገረን 2ኛ ቆሮንቶስ 5 ፥ 6 _ 8 ወገኖቼ ታድያ አሁን ከቃሉ እንደተማርነው በዚህ ጌታ በናዝሬቱ ኢየሱስ መዳን አሁን የመጣ ትምህርት ወይም ዛሬ የተገኘ አለበለዚያም ብዙዎች እንደሚሉት ከሌሎች የተኮረጀ ወይም መጤ የሆነ ሳይሆን አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳንና የተስፋ ቃል የሆነ ነው በመሆኑም ሊያድነን አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳንና የተስፋ ቃል የሆነንን ኢየሱስን የሚሽር የትኛውም ሕግ የለም ስለዚህ የምንድነው አስቀድሞ በእግዚአብሔር በተረጋገጠው ኪዳናችንና የተስፋም ቃላችን በሆነው በኢየሱስ ብቻ ነው ኢየሱስ አንድና ብቸኛ የሆነ የመዳኛ መንገዳችን ነው ከዚህ ውጪ ሌላ የመዳኛ መንገድ የለም የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ አስቀድሞ በእግዚአብሔር በተረጋገጠው ኪዳናችንና ተስፋችን በሆነው በኢየሱስ ብቻ መዳን እንዳለ የሚጠቁም ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ወይም የመጣው ሕግ የሰው ልጆችን ሕያው ሊያደርግ የሚችል አለመሆኑንና ጽድቅም በሕግ በኩል እንዳልሆነ ያመላክታል እንደገናም ይኸው ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የመጣው ሕግ የሰው ልጆችን የሚያድን ካለመሆኑም የተነሳ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚቃወም አለመሆኑንም ይጠቁመናል በመሆኑም ዛሬ በሐዲስ ኪዳን ሰዎች የሕግን ማንነትና ምንነት በትክክል ተረድተው ሊያድናቸው ወደሚችል የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ማለትም ወደ ክርስቶስ ያለጥርጥር በእርግጠኝነት ሊመጡ ይገባል ወገኖች እንግዲህ ትምህርቱ እነዚህንና የመሣሠሉትን ሁሉ በሰፊው ያብራራል ስለሆነም ከዚህ በመቀጠል በየተራ የሚለቀቁትን ቪዲዮዎች እየተከታተላችሁ በመስማት ለሌሎችም ሰዎች ሼር እንድታደርጉት ስል ከትልቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ተባረኩልኝ የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Comments

Popular posts from this blog

የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ሰባት 3ኛ) ምልክታዊ ትዕይንቶች እና እንቅስቃሴን የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንት Symbolic View and The Dynamic View

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት