እግዚአብሔር የማጣርያ ጊዜ አለው ( ( ዘፍጥረት 16 ፥ 5 እና 6 ) Part 3 የትምህርቱ ዋና ሃሳቦች እግዚአብሔር የማጣርያ ጊዜ አለው አጋር እንዳረገዘች አይታ ሣራን በዓይኗ ያቃለለቻት ቢሆንም በእግዚአብሔር የማጣርያ ጊዜ ውስጥ ገብታ መጣራት ጀመረች ለአጋር የመጣ አንዱ የሕይወት ማጣርያ 1ኛ ) በሦራ ስቃይ ምክንያት ከሦራ ፊት መኮብለልዋ ነው 2ኛ ) በዚህ ውስጥ የእግዚአብሔር መልአክ በውሃ ምንጭ አጠገብ በበረሃ አገኛት በዚህ ውስጥ የሆነውን ነገር በዘፍጥረት 16 ፥ 7 _ 16 የተጻፈውን መመልከት ነው 3ኛ ) ለአጋር የመጣው ሦስተኛው የሕይወት ማጣርያ ደግሞ ሣራ ግብጻዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን ልጅ ሲስቅ በማየቷ ይህቺን ባርያ ከነልጇ አሳድ የዚህች ባርያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና ስትል በጽኑ የውሳኔ ቃል የተገለጠችበት ቃል ነው 4ኛ ) በዚህ ውስጥ ግን የአጋር ከነልጇ መውጣት አንዱ ለአጋር የመጣ የሕይወት ማጣርያ ቢሆንም በዚህ ውስጥ ግን በነበረው ውጣ ውረድ እና አለመግባባት የሣራም ሕይወት አብሮ ተጣርቷል እንደገናም ሣራ ብቻ አይደለችም የትልቁ የቤቱ ባለቤት የሆነው የአብርሃም ሕይወትም በከፍተኛ ሁኔታ በመጣራት ላይ ነበር ዘፍጥረት 21 ፥ 11 _ 14 5ኛ) እንዳረገዘች አይታ ሣራን በዓይኗ ያቃለለችው አጋር በዚህ ከእግዚአብሔር በሆነ የመጨረሻ የሕይወት ማጣርያ በቤርሳቤህ ምድረበዳ ተቅበዘበዘች ፣ ውሃውም ከአቁማዳው አለቀ ብላቴናውንም ከአንድ ቁጥቋጦ በታች ጣለችው ፣ እርስዋም ሄደች ፦ ብላቴናው ሲሞት አልየው ብላ ቀስት ተወርውሮ የሚደርስበትን ያህል ርቃ በአንጻሩ ተቀመጠች፣ ፊት ለፊትም ተቀመጠች ቃልዋንም አሰምታ አለቀሰች ከዚህ የእግዚአብሔር የሕይወት ማጣርያ መልስ ነው እንግዲህ የእግዚአብሔር የማጽናናትና የማንሣት የጉብኝትም መልስ የመጣው 6ኛ ) የእግዚአብሔር የማጽናናትና የማንሣት ፣ የጉብኝት መልስ ዘፍጥረት 21 ፥ 17 _ 21 በዚህ ውስጥ የምንማረው እውነት ለአጋር ማርገዝ የመጨረሻ መስሏት ሣራን እስከማቃለል ያድርሳት እንጂ ይህ ማርገዝ ለአጋር የመጨረሻ ደረጃ አይደለም አጋር ገና ጀመረች እንጂ ያልጨረሰች በመሆንዋ ከፊት ለፊቷ ብዙ የሚጠብቃት ሴት ነበረች ይህንን ባለማወቋ ግን ፍየል ከመድረስዋ ቅጠል መበጠስዋ እንደሚባለው ገና ከማርገዟ የቤቱ እማ ወራ ሆና ሁሉን የያዘችና የጨበጠች መስሏት አልፋ ሄዳ ሣራን ማቃለል ጀመረች ታድያ ወደዚህ ነገር የከተታት ለማርገዝ ስትል የተጠቀመችው አቋራጭ መንገድ ነው ወገኖቼ አቋራጭ መንገድ አጋርን ብቻ ሳይሆን ዛሬም እኛን ሁላችንንም ብዙ የማያስፈልግ ነገር ውስጥ ይከተናል የአጋር ሣራን ማቃለል ችግሩ ማርገዙ ብቻ ሳይሆን አቋራጭ መንገድንም ጭምር መጠቀሙ ነው ዛሬም ታድያ በአቋራጭ መሰላል ተወጣጥተው ጸነስን አረገዝን የቤትም ባለቤት ሆንን በሚል ሰበብ አጠገባቸው ላለው የማቃለል ምክንያትና መነሾ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ወደዚህ አጉራ ዘለል ድርጊት የከተታቸው ነገር የሄዱበት አቋራጭ መንገዳቸውና ለመድረስ ሲሉም የተውጣጡበት መሰላላቸው ነው ለነገሩ ታድያ እነዚህ ሰዎች ደረስን ሲሉ ሌላውን ሊንቁና ሊያቃልሉ ይነሱ እንጂ መድረሳቸው ግን በእግዚአብሔር ዘንድ በትክክል የተረጋገጠ አይደለምና ከፊት ለፊታቸው እንደ አጋር የሚጠብቃቸው ዋይታና ልቅሶን ያዘለ የእግዚአብሔር የማጣርያ ጊዜ አለ ታድያ ይህ የማጣርያ ጊዜ አትምጣ ቢባልም እንደነዚህ ላሉ ሰዎች መምጣቱ አይቀርም ወገኖቼ ማንኛውንም የክርስትና ጉዞም ሆነ የሕይወት ጉዞ ጀመርነው እንጂ አልጭረስነውምና እንደጭረስንና እንደተመረቅንም ሆነን በሰው ፊት በመቅረብ በሌሎች ሕይወት ውስጥ ጣልቃ ገብተን ሌሎችን ከማቃለልና ከመናቅ እግዚአብሔር ይጠብቀን ሌሎችን ስናቃልልና በሌሎች ስንስቅ እኛው እራሳችን ጀመሩ ግን ሊደመድሙ አቃታቸው ተብለን በራሳችን እንዳይሳቅብን ከሌላው ላይ ነገራችንን አንስተን ለራሳችን እንትጋ የሉቃስ ወንጌል 14 ፥ 25 _ 35 እንደገናም በአቋራጭ በተገኘው ነገር የመጣው ቀረርቶአችን ውሎ ሳያድር ወደመረረ ልቅሶ ይቀየራልና አሁኑኑ ከዚህ ሽለላና ማናናቅ ወጥተን ሕይወታችንን ለዚህ ጌታ እንስጥ ጌታ በነገር ሁሉ ይርዳን

Comments

Popular posts from this blog

የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ሰባት 3ኛ) ምልክታዊ ትዕይንቶች እና እንቅስቃሴን የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንት Symbolic View and The Dynamic View

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት