Part 1 እኛ ሰዎች ፦ ለተውነው የእግዚአብሔር ሕግ መተኪያ እንፈልጋለን 1ኛ ሳሙኤል 8እኛ ሰዎች ፦ ለተውነው የእግዚአብሔር ሕግ መተኪያ እንፈልጋለን 1ኛ ሳሙኤል 8 ፥ 10 ፤ የማርቆስ ወንጌል 7 ፥ 8 እና 9 Part 1 ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር እየተዘጋጀ የሚቀርብ በጌታ አማኞች ለሆኑ ቅዱሳንና የጌታ አገልጋዮች እንዲሁም ጌታን አምኜ በሕይወቴ ማደግና መለወጥ የጌታም ትክክለኛ ደቀመዝሙር መሆን እፈልጋለሁ ለሚል ክርስቲያን ሁሉ የሚሆን ትምህርት ነው የዚህ ትምህርት ዋና ዓላማ ሰዎች የእግዚአብሔር ሕግ በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ጸንተው እንዲኖሩ እና ይህንንም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይተዉ የሕይወታቸውም መመርያ እንዲያደርጉት በጽኑ የሚናገር በመሆኑ አስፈላጊያችን ነው ይሁን እንጂ እኛ የሰው ልጆች ሰዎች እንደመሆናችን መጠን ከድካም የተነሳ አለበለዚያም ካለማወቅ የተነሳም ልንለው እንችላለን ብቻ በተፈጠሩት ልዩ ልዩ አጋጣሚዎችና ክስተቶች በራሳችንም ስሕተትና አለማመን የእግዚአብሔርን ሕግ መተው ስንፈልግ በምትኩ ሌላ ነገር እንጀምራለን ለዚህም ነው ባለፈው ባስተላለፍኩት የትምህርት ክፍለ ጊዜ ነቢዩ ኤልያስ ንጉሥ አክአብን እስራኤልን የምትገለባብጡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ትታችሁ በዓሊምን የተከተላችሁ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔ አይደለሁም ሲል የተናገረው 1ኛ ነገሥት 18 ፥ 18 የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የተዉና የሚተዉ በደጅ ያሉ ወይንም በቤቱ ውስጥ ሆነው የእግዚአብሔር ቃል ያልተገለጠላቸው ያልገባቸውም ናቸው ብለን ብዙዎቻችን ልናስብ እንችላለን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የተዉ ወይንም የሚተዉ ግን በደጅ ያሉ የመጽሐፉም ቃል ያልተገለጠላቸው ብቻ ሳይሆኑ የመጽሐፉ ቃል ተገልጦልናል ገብቶናል ትክክለኛም ክርስቲያኖች ነን የምንል አልፈንም የምናስተምር የምንሰብክ የምንዘምርና ልዩ ልዩ አገልግሎቶችንም በቤቱ የምንሰጥ ሰዎች የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመተው በምትኩ ሌላ ነገር የምንጀምርበት ሁኔታ አለ ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ በዘመኑ ለነበሩት የሕግ መምሕራን እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ ? ያለው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደማጠብ የሰዉን ወግ ትጠብቃላችሁ ይህንንም የመሠለ ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ አለ እንደገናም ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እጅግ ንቃችኋል አለ ይህ እንግዲህ በጣም አስደንጋጭና አስፈሪም የሆነ ቃል ነው የማቴዎስ ወንጌል 15 ፥ 3 ፤ የማርቆስ ወንጌል 7 ፥ 8 እና 9 እንመልከት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትቶ በምትኩ ሌላ ነገር የተከተለ በዘመኑ የነበረው ንጉሥ አክአብ እንደገናም በጊዜው በኢየሱስ ዘመን ያገለግሉ የነበሩ የመቅደስ አገልጋዮች የካህናት አለቆችና የሕግ መምሕራን ብቻ ሳይሆኑ ዛሬም ላይ ያለን ከዚህ በፊት የእግዚአብሔርን ሕግ የምናውቅና በሕይወታችንም የተለማመድን አልፈን ተርፈንም አገልግሎት የጀመርንና አስተማሪዎች ሰባኪዎችም ጭምር የሆን እስካሁንም ድረስ ጥሩ ክርስቲያን ነኝ ስንል ለራሳችንም ሰፊውን ቦታ ሰጥተን በማገልገል በመዘመር በመስበክና በማስተማር ላይ ያለን እኛም ነን ይህንንም የምናደርገው በዛሬው ሕይወታችን የእግዚአብሔርን ቃል ከመለማመዳችን እና የአገልግሎት መድረኮችንም በቀላሉ ከማግኘታችን የተነሳ ተሰለቻችተን ፣ የእግዚአብሔርም ነገር ቀሎብን ደፋሮች ፣ ደንታ ቢሶች እንዲሁም ግድ የለሶችም ሆነን ነው ታድያ ጌታ ኢየሱስ በዘመኑ የነበሩትን የሕግ መምሕራን ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እጅግ ንቃችኋል እንዳላቸው እኛንም ከዚሁ ባልተናነሰ ሁኔታ እንዲሁ እያለን ይገኛል ሕይወትና ኑሮ ያልታከለበት አገልግሎት የመድረክ ላይ ባዶ ጩኸት ነውና እኛንም ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እጅግ ንቃችኋል አስብሎናል የፈሪሳውያን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መናቅ ወደ ከፋ ነገር ወሰዳቸው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ከመናቃቸው የተነሳ ወጋቸውን ብቻ የሚጠብቁ አልሆኑም የእግዚአብሔርንም ቤት የንግድ ቤት የሸቃጮችና የለዋጮች ቤት አደረጉት በመሆኑም የእግዚአብሔር ቤት ሕጉ የሚከበርበት የሚጠበቅበትም ቤት መሆኑ ቀርቶ የሰዎች ወግ ከፍ ብሎና ንሮም የሚከበርበት በዚያው ልክም ንግዱ ፣ ሸቀጡም የተጧጧፈበት ቤት ሆነ የማቴዎስ ወንጌል 21 ፥ 12 _ 18 ዛሬም ያለው ሁኔታ ይሄ ነው የሰዎች ወግ ከእግዚአብሔር ሕግ በላይ ከፍ ብሎ ፣ በልጦና ተጠብቆ በምትኩ ግን የእግዚአብሔር ሕግ እጅግ ተንቆ በቤቱ ንግድና ሸቀጥ በሰፊው የተጀመረበት እየተስፋፋም ያለበት ጊዜ በመሆኑ እጅግ አሳዛኝ ነው የእግዚአብሔር ሕግ ለፕሮግራም መሙያ ፣ ለሰዎችም ጉዳይ ማስፈጸምያ ከሚነገር ውጪ ዛሬም ተንቆአል ሰዎች የለመዱትን መድረክ አግኝተው መድረኩና መናገሩ ሳይቀርባቸው የእግዚአብሔርን ሕግ ለተሰበሰበው ሕዝብ መስበካቸው ማስተማራቸው ነው እንጂ ግድ የሚላቸው ከሰዎች የሚያገኙትና የለመዱትም ወግ እስካልቀረባቸው ድረስ ስለእግዚአብሔር ቃል መጠበቅና አለመተው ብዙም ግድ አይሰኙም የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ በነዚህ ሃሳቦች ዙርያ ብቻ ያጠነጠነ አይደለም ከዚህም ሌላ አንዳንዶች የእግዚአብሔርን ሕግ ስንተው ምክንያት የምናደርጋቸው ብዙ ነገሮች አሉንና 1ኛ ) መጽሐፍቅዱሳችን በራሱ በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ ብቸኛ የእግዚአብሔር መጽሐፍ በመሆኑ ትክክለኛና እውነተኛ የእግዚአብሔር መጽሐፍ ነው ስለዚህ ቃሉን በተመለከተ እኛ የቃሉ አማኞች ምንም ዓይነት ምክንያት ሳንሰጥ የእናቴ ቀሚስ አወላከፈኝ በሚል ዓይነት ሰበብም ማንንም ምክንያት ሳናደርግ የተጻፈልንን ቃል ብቻ አምነንና ተከትለን ከምንሄድ ውጪ ይህንን ቃል ከነገሮች ከሰዎችና ከሁኔታዎች ጋር ማያያዝ የለብንም ልናያይዘውም አይገባም ከዚህም ሌላ ይህንኑ የመጽሐፉን ቃል በምንም ሆነ በማንም አንተካውም እንተካው ብንልም የመጽሐፉን ቃል በሌላ ለመተካት የማንችል በመሆኑ መተኪያም አናዘጋጅለትም 2ኛ) አሁንም መጽሐፍቅዱሳችን በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ ብቸኛ የእግዚአብሔር መጽሐፍ በመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕግ ለመተዋችን ማንንም ምክንያት ማድረግ እንደሌለብን ትምህርቱ ይጠቁማል 3ኛ) ሕይወታችንንም በቃሉ መመስረት እንጂ ሁሉ ነገር የአይን አምሮትና ወረት ሆኖብን የአዲስ ነገር ጀማሪዎች ፣ ፈላጊዎችም መሆን እንደሌለብን የክፍሉ ሃሳብ ያስተምራል የአዲስ ነገር ጀማሪ እግዚአብሔር ብቻ ነውና የተወደዳችሁ ወገኖቼ ይህ ማብራርያ ከዚህ በመቀጠል በዚህ በቪዲዮ ለሚለቀቁት ትምህርቶች እንደ መንደርደርያ ይሆናችኋልና የተለቀቁትን ቪዲዮዎች በመስማት ለሌሎችም ላልሰሙ ወገኖች ሼር እንድታደርጉአቸው እንድታሰሙአቸውም ስል በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ ጌታ ዘመናችሁን አገልግሎታችሁንና ሕይወታችሁንም ጭምር ይባርክ አሜን የጌታ ባርያ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ፥ 10...

Comments

Popular posts from this blog

የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ሰባት 3ኛ) ምልክታዊ ትዕይንቶች እና እንቅስቃሴን የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንት Symbolic View and The Dynamic View

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት