የእግዚአብሔርን ሕግ የሚተካ ምንም ነገር የለም ትንቢተ ኢሳይያስ 46 ፥ 8 _ 11 በዚህ ምድር ስንኖር ብዙ ነገሮች ተተካክተው አንዱ አንዱን ተክቶ ሌላው በሌላኛውም ተተክቶ ሲሰራ ተመልክተናል ወደ እግዚአብሔርና ወደ ቃሉ ስንመጣ ግን እግዚአብሔርንም ሆነ ቃሉን በሌላ ልንተካ በፍጹም የማንችል መሆናችንን ከተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል ሃሳብ ለመረዳት እንችላለን ከዚህም የተነሣ ነው እንግዲህ መዝሙረኛው ዳዊት በመዝሙር (102 )፥ 26 እና 27 ላይ እነርሱ ይጠፋሉ አንተ ግን ትኖራለህ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ እንደ መጐናጸፍያም ትለውጣቸዋለህ ይለወጡማል አንተ ግን ያው አንተ ነህ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም በማለት ይህንን የቃሉን እውነታ በክፍሉ የነገረን እርሱ ግን መቼም መች ያው ስለሆነ እርጅናና መለወጥ ሳይኖርበት ሁሉን እንደ መጐናጸፍያ ይለውጣል በትንቢተ ሚልክያስም በተመሣሣይ መልኩ እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም በማለት የተናገረን በዚህ ምክንያት ነው በመሆኑም የኛ እግዚአብሔር መለወጥ ሳይኖርበት ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ ዛሬም ሆነ ለዘለዓለም አይለወጥም ከከንፈሩም የወጣውን ቃል አይለውጥም መዝሙረኛው ዳዊት አሁንም በዚህ ጉዳይ ኪዳኔን አላረክስም ከከንፈሬም የወጣውን አለውጥም ሲል ነገረን መዝሙር ( 89 ) ፥ 34 ጌታ እግዚአብሔር ኪዳኑን ጠባቂና የተናገረውንም ቃል የማያጥፍ ስለሆነ ዳዊትን እንዳልዋሸው አንዴ በቅዱስነቴ ማልሁ አለ መዝሙር ( 89 ) ፥ 35 ስለዚህ እግዚአብሔር ተናገረ ማለት ሆነ ማለት ነው በትንቢተ ኢሳይያስም በመጀመርያ መጨረሻውን ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን ከሩቅም ሀገር ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጠራለሁ ተናግሬያለሁ እፈጽምማለሁ አስቤያለሁ አደርግማለሁ አለን ትንቢተ ኢሳይያስ 46 ፥ 8 _ 11 የተናገረና ያሰበ እንኳን ቢሆን የተናገረውንና ያሰበውን ለመፈጸምና ለማድረግ ከፍጡራን መካከል የሚችል አንድም የለም ስለተናገረና ስላሰበ ያደርጋል ማለት ደግሞ አንችልም በብዙ የሚሳነንና ውሱን የሆንን ፣ የነገውንም ጊዜያችንን እንኳ በትክክል ማወቅ የማንችል ደካማ ፍጥረቶችም ስለሆንን ለእኛ ለሰው ልጆች ይህንን ማድረግ አይሆንልንም እናስብና እንናገር ብንል እንኳን አሁንም ምላስ ሁሉ የሚዘጋበት ከመቃብርም በታች የሚሆንበት ጊዜ አለና ማሰባችንም ሆነ መናገራችን የተናገርነውም ነገር መፈጸሙና ወደ ፍጻሜም መድረሱ ከእርሱ የተነሳ ነው ተናግረው ያልተፈጸመላቸው አስበውም ያልሆነላቸው በዚህ ምድር ብዙ ሰዎች እንደነበሩና ወደፊትም እንደሚኖሩ ለሁላችንም ግልጽ የሆነ ጉዳይ ነው መጽሐፍቅዱሳችንም በዚህ ነገር ለትምህርታችን እንዲሆንልን የጠቀሳቸው ሰዎች አሉ ከነዚህም መካከል አንደኛዋ ኤልዛቤል ናት ኤልዛቤል ኤልያስን እንዲህ ስትል ተናግራው ነበር አክአብም ኤልያስ ይህን ሁሉ እንዳደረገ ነቢያትንም ሁሉ በሰይፍ እንደገደለ ለኤልዛቤል ነገራት ኤልዛቤልም ነገ በዚህ ጊዜ ነፍስህን ከነዚህ እንደ አንዲቱ ነፍስ ባላደርጋት አማልክት ይህን ያድርጉብኝ ይህንም ይጨምሩብኝ ብላ ወደ ኤልያስ መልዕክት ላከች ይልና ኤልያስም ፈርቶ ተነሣ ነፍሱንም ሊያድን ሄደ እያለ ይናገራል 1ኛ ነገሥት 19 ከቊጥር 1 ጀምሮ የተጻፈውን እንመልከት ታድያ ይህ ኤልያስ ይህች ኤልዛቤል የጊዜው ባለሥልጣን ከመሆንዋ የተነሣ ይመስላል ከላከችለት መልዕክት የተነሣ ፈርቶ ይሽሽ ይታወክና ይደናገጥ እንጂ ኤልዛቤል በአማልክቶቿ ስም ሳይቀር ተማምላ ስለተናገረች በኤልያስ ላይ የሆነ ምንም ነገር የለም ኤልያስም የሆነው ነገር የለም ይልቁንም ኤልያስ በእርሷ ላይ የተናገረው ቃል ተፈጸመ የተፈጸመውም ያ ቃል የኤልያስ ቃል ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ነው 1ኛ ነገሥት 20 ፥ 23 ፤ 2ኛ ነገሥት 9 ፥ 36 እና 37 ከኤልዛቤል ጋር በተመሳሳይ መልኩ ሐማ በመርዶክዮስ ላይ ተናግሮ ያልተፈጸመው ፣ የአሦሩ ንጉሥ ሰናክሬም በሕዝቅያስና በሕዝቅያስ አምላክ ላይ ሳይቀር ተናግሮ ያልተፈጸመለትን ይልቁንም በተቃራኒው የሆነበትን ፣ በሐዲስ ኪዳንም ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ ይናገር እንጂ የእግዚአብሔር ሃሳብ ብቻ በኢየሱስ ላይ መፈጸሙንና ሌሎችንም ከመጽሐፍቅዱሳችን ጠቅሰን መመልከት እንችላለን 2ኛ ነገሥት ምዕራፍ 18 ፣ ምዕራፍ 19 ፣ ምዕራፍ 20ን በሙሉ እንመልከት ፤ መጽሐፈ አስቴር 5 ፥ 9 _ ፍጻሜ ፤ መጽሐፈ አስቴር ምዕራፍ 6 ምዕራፍ 7 ፤ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 19 ፥ 1 _ 11 ሰዎች ካላቸው ሥልጣን ተነስተው ፣ አምባ ገነናዊና ስሜታዊም ሆነው ያሰቡትን የሚያደርጉ የተናገሩትንም የሚፈጽሙ መስሎአቸው ዛሬም ብዙ ብዙ ነገር ሊሉ ይችላሉ አሁንም ከብዙዎቹ ጥቂቶች እንደሚሉ አንጠራጠርም ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ኃይል አግኝተው ይሄንን አደርጋለሁ ያንን እፈጽማለሁ ስላሉ ብቻ በእኛ በቅዱሳን ሕይወት የሚፈጸምብንም ሆነ የሚሆንብን ምንም ነገር የለም በሕይወታችን የሚሆነው ጌታ የፈቀደው ብቻ ነው የማቴዎስ ወንጌል 10 ፥ 27 _ 32 ጌታ አምላካችን ግን በመጀመርያ መጨረሻውን ከጥንትም ያልተደረገውን የሚናገር ምክሩንም የሚያጸና ፈቃዱንም ሁሉ የሚፈጽም ነው ስለዚህ ፈቃዱና ምክሩ ሃሳቡም ያለበትን ይህንን የእርሱን ሕግ የሚተካ ምንም ነገር የለም ይልቁንም ሕጉን በሌላ ነገር ተክቼ የምፈልገውን እፈጽማለሁ ብሎ ከመነሳት ይልቅ ከእርሱ ጋር በመስማማት በጎነት እንዳለ በእግዚአብሔር ቃል የተጻፈልን በመሆኑ የኢዮብ መጽሐፍ እንዲህ ሲል ያስቀምጥልናል አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ ሰላምም ይኑርህ በዚያ በጐነትን ታገኛለህ ከአፉም ሕጉን ተቀበል በልብህም ቃሉን አኑር ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ ብትዋረድም ኃጢአትንም ከድንኳንህ ብታርቅ የወርቅን ዕቃ በአፈር ውስጥ የአፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል ሁሉን የሚችል አምላክ ወርቅና የሚብለጨለጭ ብር ይሆንልሃል የዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል ፊትሕንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ እያለ ይናገራል መጽሐፈ ኢዮብ 22 ፥ 21 _ ፍጻሜ እንመልከት ከዚህ በመቀጠል እንግዲ ይህ ለዛሬ በቪዲዮ የምንለቀው ትምህርት የሚጠቁመን የእግዚአብሔርን ሕግ የሚተካ ምንም ነገር እንደሌለ አውቀን ከሕጉ መጽሐፍ ጋር በምንስማማ ጊዜ የሕጉ መጽሐፍ በሕይወታችን ውስጥ ገብቶ የሚሰጠውን ጥቅምና የሚያመጣውን ለውጥ ወደ አምስት የሚደርሱ ዋና ዋና ነጥቦችን እንደ እግዚአብሔር ቃል በዝርዝር በማሳየት ነው ስለዚህ የእግዚአብሔር ወገኖች ቅዱሳን ትምህርቱም ከዚህ እንደሚከተለው በዚሁ በቪዲዮ አሁን የተለቀቀ በመሆኑ ሳያመልጣችሁ በመስመሩ ገብታችሁ እንድትከታተለሁ እየጋበዝኩ ይህንን ትምህርት ደግሞ መከታተል ለሚፈልጉ ሁሉ ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንድታስተላልፉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ለዘላለም ይባርካችሁ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Comments

Popular posts from this blog

የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ሰባት 3ኛ) ምልክታዊ ትዕይንቶች እና እንቅስቃሴን የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንት Symbolic View and The Dynamic View

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት