መጠራትና መመረጥ Called and Chosen ክፍል አራት

 
 መጠራትና መመረጥ



Called and Chosen  


ክፍል አራት



የመጠራትንና የመመረጥን ሃሳብ በእርግጠኝነት ያስገኘው ኢየሱስ ራሱ ነው ለደቀመዛሙርቱም ሲነግራቸው የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና ነበር ያላቸው የማቴዎስ ወንጌል 22 14 መጠራትና መመረጥ የተባሉት ሁለቱም ሃሳቦች መጽሐፍቅዱሳዊ ናቸው በእንግሊዘኛው Many are called but few are chosen ይለናል ወደ አማርኛው ስንተረጉመው  የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ማለትን የሚያመለክተን ነው የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች  ሲል ምን ማለት ነው ? ስንል የእግዚአብሔር ጥብቅ የሆነ ፍላጎቱ ለሰው ልጆች ሁሉ ደኅንነት እና የዘላለምን ሕይወት መስጠት ነው በዮሐንስ ወንጌል 3 17 ላይ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና ይለናል በዚህ በተጻፈው ቃል መሠረት ቊልፍ ቃሉ ይህንን ቢሰጠንም ነገር ግን
ሁሉም የዳነ አይደለም በዚህ ሰዓትና በዚህ ጊዜ በሮሜ 11  7-  ላይ  እንግዲህ ምንድር ነው ? እስራኤል የሚፈልጉትን አላገኙትም፤ የተመረጡት ግን አገኙት ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው ተብሎ ተጽፎአል ይለናል   በሮ  11  25 እና 26 ላይ ደግሞ ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል ይለናል ይሁን እንጂ ታድያ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው ሃሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነውና  ይህንን ሃሳቡን እግዚአብሔር በየትኛውም መንገድ ቢሆን  ይፈጽማል ኤፌሶን 1  7 እግዚአብሔር ሰውን የመረጠው የዘላለምን ሕይወት እንዲቀበል እውነትን የተማረና የተቀበለ እንደገናም በእምነት ንስሐ ገብቶ ሲጠመቅ ብቻ ነው ነገር ግን እንዴት እውነትን ከስሕተት ለይቶ ማወቅ ይችላል ? ስንል በዮሐንስ ወንጌል 17  17 ላይ በእውነትህ ቀድሳቸው ቃልህ እውነት ነው ይለናል በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ሁሉም በእርግጠኝነት የእግዚአብሔር ቃል የእውነት ምንጭ መሆኑን ማወቅና መቀበል አለበት መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም እንዲህ ይለናል እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው ይለናል 1 ጢሞቴዎስ 2  1- 4 በመሆኑም አምላካችን የሚመኘው ከልብም የሚፈልገው ሰው ሁሉ ወደ እውነተኛው የእግዚአብሔር እውቀት እንዲመጣና እንዲድን ነው








ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ቃል ይጥቀመን ይርዳን ይገናኘን አሜን

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ


ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ







Comments

Popular posts from this blog

024 ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ነው PART TWO እውነተኛ የምትወደድ ሴት ስትገኝና ኃላፊነት የሚሰማው ባል ሲገኝ ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ይሆናል ምሳሌ 18 ፥ 22 ፤ መዝሙር (128 )፥ 3 _ 4 ጋብቻችን የተበላሸ በሚሆንበት ጊዜ ህብረተሰብን ያልተወሰኑ ሥልጣኔዎችን ግንባታ ያግዳል ማኅበረሰብ ጠንካራ የሚሆነው በጋብቻና በቤተሰብ ውስጥ ነው በባልና በሚስት መካከል የተሻለ መረዳት ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት ሊኖር ይገባል [ የተባረኩ ልጆች ይፈራሉና ] ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ፤ ሮሜ 7 ፥ 2 _ 3 ፤ ኤፌሶን 5 ፥ 25 _ 32 ፤ ኤፌሶን 2 ፥ 19 _ 22 ፤ ሚልክያስ 2 ፥ 15 It was designed to be a lifelong relationship ( Romans 7 : 2 _ 3 ) that would produce godly children ( Malachi 2 : 15 ) በደስታ የሚኖሩ ተጋቢዎች አንዱና ትልቁ የእግዚአብሔር በረከት ተጋቢዎቹ የደስታ ሕይወት ውስጥ መግባታቸው ነው መክብብ 9 ፥ 9 እግዚአብሔር ዲዛይን ያደረገው ጋብቻ ተጋቢዎቹ በደስታ እንዲኖሩ የሚያደርግ ጋብቻ ነው ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ሁለት ተጋቢዎች የጋብቻን ቀለበት ሲለዋወጡ የረጅም ጊዜ ቃልኪዳን መግባታቸው ነው A lifelong commitment. Biblically speaking ,this is a covenant a solemn promise to God and one`s mate to be faithful በመጽሐፍቅዱስ አነጋገር የተከበረ ቃልኪዳን የሚባለው ተጋቢዎቹ አንድ ጊዜ ታማኝ የሆኑበት ጉዳይ ነው የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ትምህርቱ በእነዚህ ሃሳቦች ዙርያ የተካተተ በመሆኑ በኦዲዮ የተለቀቁትን ቀጣይና ተከታታይ የሆኑ ትምህርቶች በመስማት እንድትባረኩበት ለእናንተ ለአድማጮች አቅርበነዋል ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ