ሁሉም ሰው በእርግጠኝነት ንስሐ መግባት አለበት ክፍል አምስት (ሐ) All must repent

ሁሉም ሰው በእርግጠኝነት ንስሐ መግባት አለበት


ክፍል አምስት ()



All must repent



የእግዚአብሔርን መሠረታዊ እውነት ከተማረ እያንዳንዱ ሰው ንስሐ መግባት አለበት ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል 2 ጴጥሮስ 3 9 There are no exceptions God wants everyone to repent  ታድያ ሰዎች ይህንን መረዳት አንድ ጊዜ እንዴት መቀበል ይችላሉ ? ለእግዚአብሔርስ እራሳቸውን ማስገዛትና ሕይወታቸውን መለወጥ እንዴት ይችላሉ ? ጳውሎስ ሐዋርያው ይህንን ገልጾታል እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል ? ባልሰሙት እንዴት ያምናሉ ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ ? መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ ? ሮሜ 10 14 እና 15 ጳውሎስ እንደተናገረው ከእግዚአብሔር በትክክል የተላከ በእርግጠኝነት መናገር አለበት የእርሱ ታማኝ አገልጋይ ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ ሆኖ ሕጉን ካላስተማረ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ምን እንደሆነ ካልተናገረ ንስሐ የሚገባው ሰው ኃጢአትን አያቆምም የእግዚአብሔርንም ሕግ ይጥሳል ወይንም ይተላለፋል ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመጽን ደግሞ ያደርጋል ኃጢአትም ዓመጽ ነው 1 ዮሐንስ 3 4 ከዚሁ ጋር በማያያዝ በመጠራትና በመመረጥ መካከል ያለውን ልዩነት በጥቂቱም ቢሆን እንመለከታለንና ተከታተሉ እግዚአብሔር በመጀመርያ የመረጠን ለደኅንነት ነው ለዛ ጥሪ በእርግጠኝነት ምላሽ ስንሰጥ ግብዣ ለደኅንነት ይመርጠናል በ2ኛ ተሰሎንቄ 2 13 እና 14 ላይ እኛ ግን፥ በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና ለዚህም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ለማግኘት በወንጌላችን ጠራችሁ ይለናል ስለዚህ የተመረጡ ማለት ደኅንነትን ለሚያስገኘው ለእግዚአብሔር ወንጌል በእርግጠኝነት ምላሽ የሰጡ ናቸው ወገኖቼ እኛንም እግዚአብሔር ለሚፈልገን የንስሐ ሕይወትም ሆነ የመጠራትና የመመረጥ ሕይወት እንደ ቃሉ የሆነ አፋጣኝ ምላሽ የምንሰጥ ያድርገን ተባረኩልኝ ለዘላለም


Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ
                                                                              
            
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ




Comments

Popular posts from this blog

024 ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ነው PART TWO እውነተኛ የምትወደድ ሴት ስትገኝና ኃላፊነት የሚሰማው ባል ሲገኝ ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ይሆናል ምሳሌ 18 ፥ 22 ፤ መዝሙር (128 )፥ 3 _ 4 ጋብቻችን የተበላሸ በሚሆንበት ጊዜ ህብረተሰብን ያልተወሰኑ ሥልጣኔዎችን ግንባታ ያግዳል ማኅበረሰብ ጠንካራ የሚሆነው በጋብቻና በቤተሰብ ውስጥ ነው በባልና በሚስት መካከል የተሻለ መረዳት ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት ሊኖር ይገባል [ የተባረኩ ልጆች ይፈራሉና ] ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ፤ ሮሜ 7 ፥ 2 _ 3 ፤ ኤፌሶን 5 ፥ 25 _ 32 ፤ ኤፌሶን 2 ፥ 19 _ 22 ፤ ሚልክያስ 2 ፥ 15 It was designed to be a lifelong relationship ( Romans 7 : 2 _ 3 ) that would produce godly children ( Malachi 2 : 15 ) በደስታ የሚኖሩ ተጋቢዎች አንዱና ትልቁ የእግዚአብሔር በረከት ተጋቢዎቹ የደስታ ሕይወት ውስጥ መግባታቸው ነው መክብብ 9 ፥ 9 እግዚአብሔር ዲዛይን ያደረገው ጋብቻ ተጋቢዎቹ በደስታ እንዲኖሩ የሚያደርግ ጋብቻ ነው ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ሁለት ተጋቢዎች የጋብቻን ቀለበት ሲለዋወጡ የረጅም ጊዜ ቃልኪዳን መግባታቸው ነው A lifelong commitment. Biblically speaking ,this is a covenant a solemn promise to God and one`s mate to be faithful በመጽሐፍቅዱስ አነጋገር የተከበረ ቃልኪዳን የሚባለው ተጋቢዎቹ አንድ ጊዜ ታማኝ የሆኑበት ጉዳይ ነው የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ትምህርቱ በእነዚህ ሃሳቦች ዙርያ የተካተተ በመሆኑ በኦዲዮ የተለቀቁትን ቀጣይና ተከታታይ የሆኑ ትምህርቶች በመስማት እንድትባረኩበት ለእናንተ ለአድማጮች አቅርበነዋል ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ