የጌታ እራት ክፍል ሦስት በዚህ ክፍለ ትምህርት የጌታን እራት የምንጠቀመው በ1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 20 በተጻፈው ቃል መሠረት ሲሆን የጌታን እራት በምንካፈልበት ጊዜ ዓላማው ከጌታ ኃይልንና ጥንካሬን መቀበላችንን እንድናውቅ የሚያስችለን ነው እንደገናም ራሳችን ለጌታ የተሰጠን እንድንሆን ለማድረግ ነው ይህንን የጌታን እራት ስንወስድ ቅዱስ ቁርባን ወይንም በእንግሊዘኛው Holy Communion ( ሆሊኮሚኑየን ) መሆኑን እንረዳለን ከዚህም ሌላ መጽሐፍቅዱሳችን እንደሚያስተምረን ከግሪኩ ቃል የተነሳ ምስጋናም የምንሰጥበት ነው በሉቃስ ወንጌል 22 ፥ 17 _ 19 ላይ ጽዋንም ተቀበለ አመስግኖም ይህን እንካችሁ በመካከላችሁም ተካፈሉት እላችኋለሁና፥ የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ ከአሁን ጀምሮ ከወይኑ ፍሬ አልጠጣም አለ እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ ይለናል እንደገናም በ1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 24 _ 25 ላይ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ ይለናል ስለዚህ ቅዱሳን ወገኖች ሳይመሰገን የተሰጠን የጌታ እራት የለምና እኛም ...
Comments
Post a Comment