ሁሉም ሰው በእርግጠኝነት ንስሐ መግባት አለበት ክፍል አምስት (ሐ) All must repent
ሁሉም ሰው በእርግጠኝነት ንስሐ መግባት አለበት ክፍል አምስት ( ሐ ) All must repent የእግዚአብሔርን መሠረታዊ እውነት ከተማረ እያንዳንዱ ሰው ንስሐ መግባት አለበት ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል 2 ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 9 There are no exceptions God wants everyone to repent ታድያ ሰዎች ይህንን መረዳት አንድ ጊዜ እንዴት መቀበል ይችላሉ ? ለእግዚአብሔርስ እራሳቸውን ማስገዛትና ሕይወታቸውን መለወጥ እንዴት ይችላሉ ? ጳውሎስ ሐዋርያው ይህንን ገልጾታል እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል ? ባልሰሙት ስ እንዴት ያምናሉ ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ ? መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ ? ሮሜ 10 ፥ 14 እና 15 ጳውሎስ እንደተናገረው ከእግዚአብሔር በትክክል የተላከ በእርግጠኝነት መናገር አለበት የእርሱ ታማኝ አገልጋይ ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ ሆኖ ሕጉን ካላስተማረ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ምን እንደሆነ ካልተናገረ ንስሐ የሚገባው ሰው ኃጢአትን አያቆምም የእግዚአብሔርንም ሕግ ይጥሳል ወይንም ይተላለፋል ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመጽን ደግሞ ያደርጋል ኃጢአትም ዓመጽ ነው 1 ኛ ዮሐንስ 3 ፥ 4 ከዚሁ ጋር በማያያዝ በመጠራትና በመመረጥ መካከል ያለውን ል...