ምዕራፍ ሁለት ርዕስ የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ? Topic How to understand the bible ? ክፍል አንድ

ምዕራፍ ሁለት


 ርዕስ




የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ?


 Topic

How to understand the bible ?


ክፍል አንድ



1)  በትሕትና መንፈስ



እግዚአብሔር እንዲረዳን ለትሕትና መጸለይ አለብን ይህ የመጀመርያው ቃሉን የመረዳት ቁልፍ ሃሳብ ነው ነገር ግን መጽሐፉ እንደሚነግረን ወደዚህ ወደ ትሑት መንፈሱም ወደ ተሰበረ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ ይለናል ትንቢተ ኢሳይያስ 66 2 መንፈሱም ወደተሰበረ ማለት በእንግሊዘኛው Repentant spirit ማለት ነው የንስሐ መንፈስ ያለው ማለትን ያመለክተናል የእግዚአብሔር ቃል መረዳት የአዕምሮ ማስተዋል ችሎታ የማወቅ ችሎታ ብልህነት እና  የበላይነት ጉዳይ አይደለም understanding God’s word is not a matter of superior attitude   እግዚአብሔር ለእኛ በውሳኔ መረዳትን ለመስጠት ልባችንን አስተሳሰባችንን አስተያየታችንንና አቀራረባችንን ያያል በሐዋርያት ሥራ 10 34 እና 35 ላይ   ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ አለ በሉቃስ ወንጌል 10 21 እና 22 ላይ ደግሞ በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትሕ እንዲህ ሆኖአልና ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም አለ ይለናል

የእግዚአብሔርን ቃል በመረዳት ዙርያ የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ጥቅም አለው ጥቅሙም ከዚህ እንደሚከተለው ነው በሉቃስ ወንጌል 24 44 እና 45 ላይ መጽሐፉ እንዲህ ይለናል እርሱም፦ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው ይለናል ይህ ማለት እንግዲህ መጽሐፉን መያዛቸው እና መጨበጣቸው የብልህነትና የአዕምሮ ማስተዋል ችሎታቸው ጉዳይ ሳይሆን እግዚአብሔር አዕምሮአቸውን ከፍቶላቸው ነው

በ1ኛ ቆሮንቶስ 2 13 _ 14 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም ይለናል ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ቃል የገለጠው እግዚአብሔር ነው የሚጨመርለትና የሚቀነስለት መጽሐፍ ሆኖ ለመረዳትም የሰዎችን ብልህነትና የአዕምሮ ማስተዋል ግምትና ጥረትን አልጠየቀም እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ይጥቀመን ተባረኩልኝ
 


ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Comments

Popular posts from this blog

024 ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ነው PART TWO እውነተኛ የምትወደድ ሴት ስትገኝና ኃላፊነት የሚሰማው ባል ሲገኝ ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ይሆናል ምሳሌ 18 ፥ 22 ፤ መዝሙር (128 )፥ 3 _ 4 ጋብቻችን የተበላሸ በሚሆንበት ጊዜ ህብረተሰብን ያልተወሰኑ ሥልጣኔዎችን ግንባታ ያግዳል ማኅበረሰብ ጠንካራ የሚሆነው በጋብቻና በቤተሰብ ውስጥ ነው በባልና በሚስት መካከል የተሻለ መረዳት ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት ሊኖር ይገባል [ የተባረኩ ልጆች ይፈራሉና ] ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ፤ ሮሜ 7 ፥ 2 _ 3 ፤ ኤፌሶን 5 ፥ 25 _ 32 ፤ ኤፌሶን 2 ፥ 19 _ 22 ፤ ሚልክያስ 2 ፥ 15 It was designed to be a lifelong relationship ( Romans 7 : 2 _ 3 ) that would produce godly children ( Malachi 2 : 15 ) በደስታ የሚኖሩ ተጋቢዎች አንዱና ትልቁ የእግዚአብሔር በረከት ተጋቢዎቹ የደስታ ሕይወት ውስጥ መግባታቸው ነው መክብብ 9 ፥ 9 እግዚአብሔር ዲዛይን ያደረገው ጋብቻ ተጋቢዎቹ በደስታ እንዲኖሩ የሚያደርግ ጋብቻ ነው ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ሁለት ተጋቢዎች የጋብቻን ቀለበት ሲለዋወጡ የረጅም ጊዜ ቃልኪዳን መግባታቸው ነው A lifelong commitment. Biblically speaking ,this is a covenant a solemn promise to God and one`s mate to be faithful በመጽሐፍቅዱስ አነጋገር የተከበረ ቃልኪዳን የሚባለው ተጋቢዎቹ አንድ ጊዜ ታማኝ የሆኑበት ጉዳይ ነው የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ትምህርቱ በእነዚህ ሃሳቦች ዙርያ የተካተተ በመሆኑ በኦዲዮ የተለቀቁትን ቀጣይና ተከታታይ የሆኑ ትምህርቶች በመስማት እንድትባረኩበት ለእናንተ ለአድማጮች አቅርበነዋል ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ