የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ? ክፍል ሦስት በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት በመፈለግ

የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ?

 
 


ክፍል ሦስት


በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት በመፈለግ


አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም
አቤቱ፥ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቍጣ አይሁን ትንቢተ ኤርምያስ 10 23 _ 24



በትሕትና የእግዚአብሔርን እርማት የምንፈልግበት ምክንያት የሰው መንገድ ከራሱ አይደለም እንደገናም አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም ስለሚለን ለአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለሁል ጊዜ በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት ለሕይወታችን እንፈልጋለን መጽሐፍቅዱሳችን በሮሜ 8 6 _ 9  ላይ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም ይለናል በሥጋ ስናስብ ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ጠበኞች ነን ለእግዚአብሔርም ሕግ አንገዛም እንገዛ ብንልም እንኳ የሚሳነን ሆነን እንገኛለን እግዚአብሔርንም ማስደሰት አንችልም ለዚህ ነው ኤርምያስ በትንቢቱ አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም በማለት ሳያበቃ በሥጋ የተጓዘባቸው መንገዶች አካሄዱንም ለማቅናት የተራመደበት ጐዳናዎች  ቅጣትን እንዳመጡበት የተገነዘበ በመሆኑ አቤቱ፥ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቍጣ አይሁን ሲል አምላኩን የተማጸነው ከዚህ የተነሳ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ዘንድ መኖሩ አስፈላጊነቱ ለዚህ ነው በመንፈስ እንጂ በሥጋ እንድንሆን አያደርገንም እንደገናም የእርሱ የእግዚአብሔር ወገን ለመሆናችን በውስጣችን ያለው የክርስቶስ መንፈስ ያረጋግጥልናል ሌላው በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት የምንፈልግበት ምክንያት እግዚአብሔር ፍጹማን ሊያደርገን ስለሚፈልግ ነው በማቴዎስ ወንጌል 5 48 ላይ እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ ይለናል ስለዚህ አባታችን ፍጹም ወደ ሆነበት የፍጽምና ሕይወት ለመምጣት የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት በትሕትና መፈለግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ለዚህ ነው በትንቢተ ኢሳይያስ 66 2 ላይ እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ ያለን እንደገናም በዚሁ በትንቢተ ኢሳይያስ 66 5 ላይ በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ  ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር ብለዋል ነገር ግን ያፍራሉ ይለናል ስለዚህ በመጥላትና በማሳደድ ሕይወት ውስጥ ሆነን እና  እግዚአብሔርም ሲከብር አይተን ከሚያፍሩት ወገኖች ከምንሆን ይልቅ በትሕትና እና በተሰበረ መንፈስ በቃሉ ወደምንንቀጠቀጥበት ሕይወት መጥተን እግዚአብሔር ቢመለከተን ለእኛ እጅግ የተሻለ ነው መዝሙረኛው ዳዊት በቃሉ ወደሚንቀጠቀጥበት ሕይወት ስለመጣ ራሱን እና ማንነቱን በሙሉ ለተገለጠው ለእግዚአብሔር ቃል አሳልፎ በመስጠት አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ  አለ መዝሙር 138 (139) 23 እና 24 ታድያ እኛም እንደ ዳዊት በዘላለም መንገዱ እንድንመራ ለተገለጠው ለእግዚአብሔር ቃል እራሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥና ሕይወታችንንም ለእርሱ እንድናስመረምር በእጅጉ ያስፈልገናል እግዚአብሔር ለዚህ ይርዳን ከዚህ በመቀጠል ጥቂት ከዚህ በመቀጠል ጥቂት ሃሳቦችን በእንግሊዝኛ ለተጨማሪ ማብራርያነት ይበልጥ እንዲረዳ መስጠት እፈልጋለሁና ተከታተሉ ጌታ ይባርካችሁ

Keep an open mind

Be willing to admit when you are wrong and change even if it means letting go of a long held belief or tradition. If u can successfully apply this one principle you will be for a head in the search for spiritual truth. Act 17 : 11, Isaiah 8 : 20.

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
  1. 'My Lord Jesus is my Savior'

Comments

Popular posts from this blog

024 ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ነው PART TWO እውነተኛ የምትወደድ ሴት ስትገኝና ኃላፊነት የሚሰማው ባል ሲገኝ ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ይሆናል ምሳሌ 18 ፥ 22 ፤ መዝሙር (128 )፥ 3 _ 4 ጋብቻችን የተበላሸ በሚሆንበት ጊዜ ህብረተሰብን ያልተወሰኑ ሥልጣኔዎችን ግንባታ ያግዳል ማኅበረሰብ ጠንካራ የሚሆነው በጋብቻና በቤተሰብ ውስጥ ነው በባልና በሚስት መካከል የተሻለ መረዳት ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት ሊኖር ይገባል [ የተባረኩ ልጆች ይፈራሉና ] ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ፤ ሮሜ 7 ፥ 2 _ 3 ፤ ኤፌሶን 5 ፥ 25 _ 32 ፤ ኤፌሶን 2 ፥ 19 _ 22 ፤ ሚልክያስ 2 ፥ 15 It was designed to be a lifelong relationship ( Romans 7 : 2 _ 3 ) that would produce godly children ( Malachi 2 : 15 ) በደስታ የሚኖሩ ተጋቢዎች አንዱና ትልቁ የእግዚአብሔር በረከት ተጋቢዎቹ የደስታ ሕይወት ውስጥ መግባታቸው ነው መክብብ 9 ፥ 9 እግዚአብሔር ዲዛይን ያደረገው ጋብቻ ተጋቢዎቹ በደስታ እንዲኖሩ የሚያደርግ ጋብቻ ነው ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ሁለት ተጋቢዎች የጋብቻን ቀለበት ሲለዋወጡ የረጅም ጊዜ ቃልኪዳን መግባታቸው ነው A lifelong commitment. Biblically speaking ,this is a covenant a solemn promise to God and one`s mate to be faithful በመጽሐፍቅዱስ አነጋገር የተከበረ ቃልኪዳን የሚባለው ተጋቢዎቹ አንድ ጊዜ ታማኝ የሆኑበት ጉዳይ ነው የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ትምህርቱ በእነዚህ ሃሳቦች ዙርያ የተካተተ በመሆኑ በኦዲዮ የተለቀቁትን ቀጣይና ተከታታይ የሆኑ ትምህርቶች በመስማት እንድትባረኩበት ለእናንተ ለአድማጮች አቅርበነዋል ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ