መጽሐፍቅዱስ በራሱ ሲተረጐም Let the Bible interpret Itself ክፍል ሁለት
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ መጽሐፍቅዱስ በራሱ ሲተረጐም Let the Bible interpret Itself ክፍል ሁለት መጽሐፍቅዱስን በራሱ የምንተረጒምበት ፣ ከሰዎች ፣ ከነገሮች ፣ ከሁኔታዎች እና ከመሣሠሉት ጋርም የማናያይዝበት ምክንያት በ2ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 20 ላይ በተጠቀሰው ቃል መሠረት ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ ስላልመጣና ይህንን የትንቢት ቃል ቅዱሳንም በመንፈስቅዱስ ተነድተው ስለተናገሩት ነው የክፍሉ ሃሳብ እንዲህ ይለናል ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ በማለት ይጠቁመናል ለዚህም ነው ጴጥሮስ አሁንም ከገናናው ክብር በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ በማለት የተናገረው ስለዚህ ይህ የትንቢት ቃል በቅዱሱ ተራራ ከተነገረው ከገናናው ክብር በእርሱ ደስ ...