Topic Teaching የትምህርት ርዕስ Different responses of those who understand ከተረዱ ሰዎች የሚመጡ ልዩ ልዩ መልሶች ክፍል ሰባት

ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር                                                                      በጌታ አማኞች ለሆኑ ቅዱሳንና የእግዚአብሔር አገልጋዮች እየተዘጋጀ የሚቀርብ  ተከታታታይ ትምህርት ነው


Topic Teaching

የትምህርት ርዕስ

Different responses of those who understand

ከተረዱ ሰዎች የሚመጡ ልዩ ልዩ መልሶች


ክፍል ሰባት


እግዚአብሔር ሦስት ዓይነት ምላሽ የሚሰጡ ሰዎችን እንደቃሉ አስቀምጦልናል ከእነዚህ ማነው ትክክለኛ መረዳት ያለው ? ስንል እግዚአብሔር አዕምሮን ከፍቷል ትርጉሙን ይዘዋል ጨብጠውማል ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተለያዩ መልሶችን ሰጥተዋል

  በማቴዎስ ወንጌል 13 21 ላይ በጭንጫ ላይ የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ ወዲያው በደስታ የሚቀበለው ነው ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም በቃሉም ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል ይለናል
       
    ይህ ሰው በመጀመርያ የተቀበለውን ደስታ መለሰ ነገር ግን በፍጥነት ወደኋላ አለ ለምን ወደኋላ አለ ?  ስንል ከሌሎች ሰዎች የመከራ ጫና እና ክብደት የተነሳ ማለትም ካልተረዱ ሰዎች በሚነሳ መከራ ነው እርሱ የሚጨነቀው እግዚአብሔር ከሚያስበው በላይ ይበልጥ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ነው በጀልባ ውስጥ ያለውን ቋጥኝ ይፈራል በዙርያው ያሉ ሰዎች ለእርሱ ማረጋገጫዎችና ጠቃሚዎች ናቸው ረብሻና ማሳደድ ለእግዚአብሔር በመኖር ባለ ልምምድ እርሱን የሚያደናቅፉት ናቸው ከዚህ የተነሳም ከእግዚአብሔር የተጠራበትን መጠራት ሊቀበል ይቸገራል መቀበልም ያቅተዋል አይቀበልምም

  በማቴዎስ ወንጌል 13 22 ላይ ደግሞ በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው የዚህም ዓለም ሃሳብና የባለጠግነት ማታለል ቃሉን ያንቃል የማያፈራም ይሆናል ይለናል
   
    በዚህ ሰው ሕይወት ውስጥ የምንመለከተው አንድ እውነት ይህ ሰው ቀረብ ብሎ ያየው የራሱ አስተያየት ወይም ግምት አያሳስበውም ነገር ግን እርሱ ሌላ ችግር አለው እርሱም ስስት ነው የራሱን ምቾት በብዙ ይጠብቃል የተሻለ ማዕረግም ለማግኘት ራሱን ይንከባከባል የራሱን ጊዜና ኃይል ፍላጐት ፍጆታው ያደርጋል ለእግዚአብሔር ጊዜ የለውም ራሱን በማገልገል በጣም ቢዚና ጊዜም የሌለው ነው ከመንፈሳዊ ነገሮች ይልቅ ቁሳዊ ነገሮች ለእርሱ ይበልጥ ጠቃሚ ናቸው የእግዚአብሔርን ጥሪ በፍጹም አይቀበልም

 
  በማቴዎስ ወንጌል 13 23 መሠረትም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል ይላል
     
   ይህ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል የተረዳ ነው እንደገናም ቃሉን በቁምነገር የወሰደ ነው ይህ ሰው ለደኅንነት የተመረጠ ነው እግዚአብሔርንም የሕይወቱ መጀመርያ ያደረገ ነው በፊልጵስዩስ 2 13 መሠረት ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና ይለናል ብዙ ሰው ተጠርቷል ነገር ግን ጥቂቱ መልስ ይሰጣል ጥቂቶቹም በእውነት ንስሐ የሚገቡና ሕይወታቸውንም ለእግዚአብሔር ፈቃድ በማስገዛት ለእግዚአብሔር የትዕዛዛቱ ቃል ለመታዘዝ ቃል የገቡ ናቸው እነዚያም ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ የሚሰጡ በእግዚአብሔርም የተመረጡ ናቸው ለእርሱ ለመታዘዝና እርሱን ለማገልገል መመረጥ በእግዚአብሔር መመረጥ ነው እርሱንም  መጀመርያ ማድረግ ነው ጌታ እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ይጥቀመን ከዚህ በመቀጠል  የዘማሪ ፓስተር እንዳለ ወልደ ጊዮርጊስ ይፈውስ ይዳሰኝ እጅህ  የሚለውን የቪዲዮ መዝሙር እጋብዛችኋለሁ
  

የትምህርቱ አዘጋጅ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ


            ተባረኩልኝ

Comments

Popular posts from this blog

024 ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ነው PART TWO እውነተኛ የምትወደድ ሴት ስትገኝና ኃላፊነት የሚሰማው ባል ሲገኝ ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ይሆናል ምሳሌ 18 ፥ 22 ፤ መዝሙር (128 )፥ 3 _ 4 ጋብቻችን የተበላሸ በሚሆንበት ጊዜ ህብረተሰብን ያልተወሰኑ ሥልጣኔዎችን ግንባታ ያግዳል ማኅበረሰብ ጠንካራ የሚሆነው በጋብቻና በቤተሰብ ውስጥ ነው በባልና በሚስት መካከል የተሻለ መረዳት ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት ሊኖር ይገባል [ የተባረኩ ልጆች ይፈራሉና ] ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ፤ ሮሜ 7 ፥ 2 _ 3 ፤ ኤፌሶን 5 ፥ 25 _ 32 ፤ ኤፌሶን 2 ፥ 19 _ 22 ፤ ሚልክያስ 2 ፥ 15 It was designed to be a lifelong relationship ( Romans 7 : 2 _ 3 ) that would produce godly children ( Malachi 2 : 15 ) በደስታ የሚኖሩ ተጋቢዎች አንዱና ትልቁ የእግዚአብሔር በረከት ተጋቢዎቹ የደስታ ሕይወት ውስጥ መግባታቸው ነው መክብብ 9 ፥ 9 እግዚአብሔር ዲዛይን ያደረገው ጋብቻ ተጋቢዎቹ በደስታ እንዲኖሩ የሚያደርግ ጋብቻ ነው ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ሁለት ተጋቢዎች የጋብቻን ቀለበት ሲለዋወጡ የረጅም ጊዜ ቃልኪዳን መግባታቸው ነው A lifelong commitment. Biblically speaking ,this is a covenant a solemn promise to God and one`s mate to be faithful በመጽሐፍቅዱስ አነጋገር የተከበረ ቃልኪዳን የሚባለው ተጋቢዎቹ አንድ ጊዜ ታማኝ የሆኑበት ጉዳይ ነው የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ትምህርቱ በእነዚህ ሃሳቦች ዙርያ የተካተተ በመሆኑ በኦዲዮ የተለቀቁትን ቀጣይና ተከታታይ የሆኑ ትምህርቶች በመስማት እንድትባረኩበት ለእናንተ ለአድማጮች አቅርበነዋል ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ