Topic Teaching የትምህርት ርዕስ They must remain faithful People በእርግጠኝነት የቀሩ ታማኝ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው ትምህርት ስምንት
ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር በጌታ አማኞች ለሆኑ ቅዱሳንና የእግዚአብሔር አገልጋዮች እየተዘጋጀ የሚቀርብ ተከታታታይ ትምህርት ነው Topic Teaching የትምህርት ርዕስ They must remain faithful People በእርግጠኝነት የቀሩ ታማኝ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው ትምህርት ስምንት ጌታ እግዚአብሔር አቅርቦትና ዕድል የሰጣቸው ሰዎች በሰጣቸው ጊዜ ጌታን እንዲያገለግሉት ነው ምርጫውም የእነርሱ ነው ( ምርጫውም በቀላሉ የአንድ ቀን ምርጫ ወይም ውሳኔ አይደለም ) በእርግጠኝነት ቃል የሚገቡትና የሚመርጡት እስከመጨረሻው ነው መጽሐፉም እስከመጨረሻው የሚጸና እርሱ ይድናል በማለት ነው የሚነግረን የማቴዎስ ወንጌል 24 ፥ 13 እንደገናም ያየሃቸው አሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታት ናቸው ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ እነዚህ አንድ ሃሳብ አላቸው ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ እነዚህ በጉን ይወጋሉ በጉ...