016 የትምህርት ርዕስ እግዚአብሔር በጋብቻ ውስጥ ዓላማ አለው God’s Purpose in Marriage የክፍል ሁለት ቀጣይ ትምህርት ቊጥር ፪ በጋብቻ ውስጥ 1ኛ )ሚስቶችን ለአንድ ነገር ልናደርጋቸው መሞከር የለብንም ይህንን ስናደርግ እንሳሳታለን የጋብቻችን ውጤትም ጥፋት ይሆናል _ አብርሃም በሣራ የተሳሳተበት ጊዜ ነበር _ ሦራም አብራምን ፦ እነሆ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ ምናልባት ከእርስዋ በልጅ እታነጽ እንደሆነ ወደ እርስዋ ግባ አለችው ዘፍጥረት 16 ፥ 2 _ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባርያዋን አጋርን ወስዳ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው ዘፍጥረት 16 ፥ 3 _ ሦራም አብራምን፦ መገፋቴ በአንተ ላይ ይሁን እኔ ባሪያዬን በብብትህ ሰጠሁህ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እኔን በዓይንዋ አቃለለችኝ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ አለችው ዘፍጥረት 16 ፥ 5 _ ይህም ነገር በአብርሃም ዘንድ ስለ ልጁ እጅግ ችግር ሆነበት ዘፍጥረት 21 ፥ 11 2ኛ ) እንደ እግዚአብሔር ቃል ነገሮችን ማየት እና ማመዛዘን አለብን ( 1ኛ ጴጥሮስ 4 ፥ 11 ) 3ኛ ) ሚስቶቻችን የተፈጥሮ ችሎታቸው በፍላጎቶቻቸው ላይ እንዲሆን ማበረታታት አለብን 4ኛ ) ችሎታ ስላላቸው ደግሞ ያሹትን ሁሉ ለማግኘት እኛ ባሎች መግፋትና ማነሣሣት የለብንም 5ኛ ) የእግዚአብሔር ቃል ተከታዮች ስለሆንን ባል ቦታ አለው ሚስት ቦታ አላት 6ኛ ) ሚስቶችም ሆኑ ባሎች ትክክለኛ ቦታቸውን ሲይዙ የትውልድ ሁሉ ምሣሌ ይሆናሉ ትንቢተ ( ኢሳይያስ 51 ፥ 2 ) 7ኛ ) ትክክለኛ የሚስትነትን ቦታ ይዛ የምትንቀሳቀስ ሚስት ባልዋን አትንቅም ( ኤፌሶን 5 ፥ 33 ) 8ኛ ) ሚስት ለባልዋ ሚስት ሆና ስትመጣ ባለቤት አላት ስለዚህ ለባልዋ ትገዛ ሲል ቃሉ ራስዋን ለባልዋ ትስጥ ማለቱ ነው ኤፌሶን 5 ፥ 22 ፣ 24 ፤ ቆላስያስ 3 ፥ 18 9ኛ ) ሚስቶች በሚፈልጉትና በተገለጠላቸው ነገር ዝንባሌ እንዲያደርጉ እኛ ባሎች ማበረታታት አለብን መጽሐፈ መሣፍንት 5 ፥ 7 ፣ 12 ፣ 24 _ 29 10ኛ) ሚስቶች ከኃላፊነት ብዛትና ጫና ፣ ከሥራም ብዛት የተነሣ ሰውነታቸው ቢጎሳቆልና ቢጠቋቊሩ ራሳቸውን ለትዳራቸው ከመስጠት የተነሳም በቤት ውስጥ ባለ ተግባር ሳይቀር የቤታቸው ፣ የኑሮአቸውና የትዳራቸው ባርያ አድርገው ራሳቸውን በመቁጠር ለዚሁ ሕይወት መሳካት ጐንበስ ቀና እያሉ ቀንና ሌሊት ደፍ ደፍ ቢሉም ለእኛ ለባሎች ግን ዛሬም አስደናቂ ሚስቶች ፣ እናቶች ፣ ልዕልቶችና ንግሥቶች መሆናቸውን ልናውጅላቸው ፣ ልንናገራቸው በተግባርም ልንገልጽላቸው ይገባል ፍቅር ለዘወትር አይወድቅምና 1ኛቆሮንቶስ 13 ፥ 8 የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Comments

Popular posts from this blog

የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ሰባት 3ኛ) ምልክታዊ ትዕይንቶች እና እንቅስቃሴን የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንት Symbolic View and The Dynamic View

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት