001 የትምህርት ርዕስ ለጋብቻ ያለ መሠረት Part one  በጋብቻ ውስጥ ያለ ጠንካራ ግንኙነትን መመስረትና መገንባት የሚቻለው ሁለቱም ተጋቢዎች የሆኑ ባልና ሚስት በጣም በፍጥነት የእግዚአብሔርን ሕግ መቀበልና መለማመድ ሲችሉ ነው  የእግዚአብሔርን ሕግ ስንቀበልና ስንለማመድ ደግሞ ጋብቻችንን ከመመስረትና ከመገንባት ባሻገር ካለፈውም ኃጢአት ተመልሰን እግዚአብሔርን መታዘዝ እንጀምራለን በዚህ ውስጥም ዘላለማዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ደስታ እናገኛለን ሕዝቅኤል 18 ፥ 21 ፤ የሐዋርያት ሥራ 2 ፥ 36 ፤ የሐዋርያት ሥራ 26 ፥ 18  ጌታ እግዚአብሔር ከባልና ሚስቱ ከእያንዳንዳቸው ለእርሱ የሚጠብቀው በሚያሳስበው በጋብቻ ፈተናዎቻቸው ውስጥ የሚሰጡትን ምላሽ ነው  መጽሐፉም በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው ይለናልና ያዕቆብ 4 ፥ 17  እንደገናም ቢቻል ሁለቱ ባይቻል ግን ከሁለቱ አንዱ ማለትም ባል አለበለዚያም ሚስት ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር መለኪያ ከሰጡ እግዚአብሔር አምላክ ሁለቱንም ተጋቢዎች ሊባርካቸው በር ይከፍታል 1ኛ ቆሮንቶስ 7 ፥ 13 _ 14  እርግጠኛና የማያጠራጥር ፍቅር ለእግዚአብሔር የመታዘዝ ምሳሌ ነው በባል ወይም በሚስት ባለ ተጽእኖ እግዚአብሔርን ማስደሰት መፈለግ ይመጣል 1ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 1 _ 4  አንድ ሰው ልዩነት ሊያመጣ ይችላልና One person can make a difference የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቶቹ እንግዲህ በእነዚህና በመሳሰሉት ሃሳቦች የተጠቃለሉ ናቸው ከዚህ በመቀጠል ይህንኑ በሰፊው የሚያብራራ በኦዲዮ የተለቀቀ ትምህርት ስላለ ይህንኑ በተከታታይ የቀረበ ትምህርት ሳያመልጥዎ እንዲከታተሉ በጌታ ፍቅር ልናሳስብዎ እንወዳለን የጌታ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

Comments

Popular posts from this blog

የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ሰባት 3ኛ) ምልክታዊ ትዕይንቶች እና እንቅስቃሴን የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንት Symbolic View and The Dynamic View

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት