Posts

Showing posts from 2014
የመናኙ ሰው ዕድል ፈንታ ክርስቶስ ሆነ   ክፍል ሦስት     በክፍል ሦስት የአባ ዘውዱ ኪዳኑን ምስክርነት የምንመለከተው ስለ መብቃት ስለ መዝጋትና ወደ ጌታ ስለመጡበት ጉዳይ ነው የምንመለከተው ቅዱሳን በማስተዋል ሆናችሁ የምስክርነቱን መጨረሻ ተከታተሉ አባ ዘውዱ ኪዳኑ ምስክርነታቸውን ሲቀጥሉ እንዲህ ነበር ያሉት መገለጥ ለማግኘት ትንቢት ለመናገር መብቃት ይጠይቃል በእርግጥም ደግሞ እንደነዚህ ዓይነት ስጦታ ያላቸው ሰዎች በገዳሙ ውስጥ ከሃያና ከሰላሣ ዓመታት በላይ ያሳለፉ ናቸው ወደ ገዳሙ ለሚመጡ አዳዲስ መናንያንም በጸሎት ተጋድሎ ሲያደርጉና አቅጣጫን ሲያሳዩ የቆዩ ናቸው ሆኖም በገዳማት ውስጥ ትንቢት ከመናገር ያለፈ የብቃት ደረጃ አለ   ከሣቴ ብርሃን ፦ ምን ዓይነት ? የብቃቱ አረጋጋጭስ ማነው ?   አባ ዘውዱ ፦ የመብቃቱ እርግጠኛነት አስቀድሞ የሚመጣው ከራሱ ከግለሰቡ ነው ምክንያቱም አንድ ባሕታዊ የቱንም ያህል ዓመታት በገዳም ውስጥ ቢቆይ እርሱ ራሱ ልዘጋ ነው ብሎ ካልተናገረ ወደዚህ ብቃት መድረሱ አይታወቅም   ከሣቴ ብርሃን ፦ ልዘጋ ነው ማለት ምን ማለት ነው ?   አባ ዘውዱ ፦ አንድ ባሕታዊ ጭራሹኑ ከቤቱ ላለመውጣት የሚወስነው ውሳኔ ነው እነርሱ እንደ ኮሚቴ ዓይነት ናቸው አንድ ባሕታዊ የመዝጋት ጥያቄ ሲያቀርብላቸውም እገሌ ልዘጋ ነው ብሎ ጠይቋል ብለው ይሰበሰባሉ ኮሚቴዎቹ እንደ ዋና...