ለቅዱስን የታዘዘ ወቅታዊ መልዕክት ክፍል ሦስት እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፦ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው ? በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ በልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጅቻለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ አለው ሳሙኤልም እንዴት እሄዳለሁ ? ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል አለ 1 ኛ ሳሙኤል 16 ፥ 1 እና 2 የተወደዳችሁ ወገኖች በክፍል ሦስት ትምህርታችን ላይ የምንመለከተው የመጨረሻና የማጠቃለያ ሃሳብ ነው « ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል » ሳሙኤል ለምን ይህንን ሃሳብ መናገር ወደደ ? ሳኦል ምንድነው የሰማው ? ወደ ግድያስ ያደርሱታል ተብለው የሚታሰቡት ነገሮች ምንና ምን ናቸው ? የሚሉትንና የመሣሠሉትን ጥያቄዎች ስናነሳ መልሳችንን ከዚሁ ከመጽሐፍቅዱሳችን እናገኛለን የእሴይ ልጅ የዳዊት መቀባት ለሳኦል እንግዳ ሃሳብ አይደለም የሚቀባው የእሴይ ልጅ ዳዊት እንደሆነ ለሳኦል በግልጽነት ባይታወቀውና ባይነገረውም በምትኩ ግን ንጉሥ ይሆን ዘንድ የሚቀባ ሰው እንዳለ ለሳኦል ተነግሮታል ይህንንም ሃሳብ የምናገኘው በ1ኛ ሳሙኤል 13 ፥ 14 ...
Comments
Post a Comment