Yonas Asfaw : የመናኙ ሰው ዕድል ፈንታው ክርስቶስ ሆነ Part Two Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps December 11, 2014 Yonas Asfaw : የመናኙ ሰው ዕድል ፈንታው ክርስቶስ ሆነ Part Two: የመናኙ ሰው ዕድል ፈንታው ክርስቶስ ሆነ Part Two የተወደዳችሁ ወገኖች የአባ ዘውዱ ኪዳኑን ምስክርነት ክፍል አንድ ማቅረቤ ይታወሳል ክፍል ሁለ... Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Comments
የመልዕክት ርዕስ ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል February 05, 2015 ለቅዱስን የታዘዘ ወቅታዊ መልዕክት ክፍል ሦስት እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፦ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው ? በቀንድህ ዘይቱን ሞልተህ ሂድ በልጆቹ መካከል ንጉሥ አዘጋጅቻለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ አለው ሳሙኤልም እንዴት እሄዳለሁ ? ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል አለ 1 ኛ ሳሙኤል 16 ፥ 1 እና 2 የተወደዳችሁ ወገኖች በክፍል ሦስት ትምህርታችን ላይ የምንመለከተው የመጨረሻና የማጠቃለያ ሃሳብ ነው « ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል » ሳሙኤል ለምን ይህንን ሃሳብ መናገር ወደደ ? ሳኦል ምንድነው የሰማው ? ወደ ግድያስ ያደርሱታል ተብለው የሚታሰቡት ነገሮች ምንና ምን ናቸው ? የሚሉትንና የመሣሠሉትን ጥያቄዎች ስናነሳ መልሳችንን ከዚሁ ከመጽሐፍቅዱሳችን እናገኛለን የእሴይ ልጅ የዳዊት መቀባት ለሳኦል እንግዳ ሃሳብ አይደለም የሚቀባው የእሴይ ልጅ ዳዊት እንደሆነ ለሳኦል በግልጽነት ባይታወቀውና ባይነገረውም በምትኩ ግን ንጉሥ ይሆን ዘንድ የሚቀባ ሰው እንዳለ ለሳኦል ተነግሮታል ይህንንም ሃሳብ የምናገኘው በ1ኛ ሳሙኤል 13 ፥ 14 ... Read more
የትምህርት ርዕስ የጌታ እራት ክፍል አንድ June 26, 2015 የትምህርት ርዕስ የጌታ እራት ክፍል አንድ የተወደዳችሁ ወገኖች በቅድሚያ የጌታ ጸጋና ሰላም ለሁላችሁ ይሁን እያልኩ ሰላምታዬን በማስቀደም ስጀምር ከዚህ በመቀጠል ግን ወደዚህ ወደምጀምረው አዲስ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ከመምጣቴ በፊት በኦድዮ የሚተላለፍ በፓወር ፖይንት የተደገፈ የጋብቻ ትምህርት መጀመራችን ይታወሳል እርሱ እንዳለና እንደተጠበቀ ሆኖ በተከታታይ የሚቀጥልና የሚቀርብ ሲሆን ከዚሁ ጋራ ግን ጐን ለጐን ይህን የጌታ እራት ትምህርት በጽሑፍ ለእናንተ ለአንባቢዎች ለማቅረብና አብሬም ለማስኬድ ስለፈለግሁ ነው ወገኖች እንግዲህ ሁለቱም ትምህርቶች በጣም ጠቃሚ የሆኑ ፣ ልንከታተላቸውና እንደሚገባም ልናውቃቸው የሚገቡ ትምህርቶች ናቸው የጎደልነውና በእጅጉም የተጐዳነው በእነዚህ አንጋፋ በሆኑ ሁለት ትምህርቶች ማለትም 1 ኛ ) የጌታን እራት ምስጢር ጠንቅቆ አለማወቅና ለዚያም እውነት አለመኖር 2 ኛ ) የትዳር ትምህርት ጉድለት እንዲሁም የመረዳት ማነስና አለማወቅ ነው እንግዲህ ጌታ በረዳን መጠን እነዚህን ሁለት የትምህርት አርዕስቶች ይዘን ለእናንተ ይህንን ትምህርት በማስተዋል ለምትከታተሉ ሁሉ የምናቀርበው ይሆናል እንዳልኳችሁ የጋብቻው ትምህርት በኦድዮ የሚተላለፍ ሲሆን የጌታ እራት ትምህርት ግን በጽሑፍ በተከታታይ ለእናንተ ለአንባቢዎች የማቀርበው ነው የጌታ እራት ቅዱስ ቁርባን ማለት ሲሆን በእንግሊዘኛው ... Read more
የጌታ እራት ክፍል ሦስት July 01, 2015 የጌታ እራት ክፍል ሦስት በዚህ ክፍለ ትምህርት የጌታን እራት የምንጠቀመው በ1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 20 በተጻፈው ቃል መሠረት ሲሆን የጌታን እራት በምንካፈልበት ጊዜ ዓላማው ከጌታ ኃይልንና ጥንካሬን መቀበላችንን እንድናውቅ የሚያስችለን ነው እንደገናም ራሳችን ለጌታ የተሰጠን እንድንሆን ለማድረግ ነው ይህንን የጌታን እራት ስንወስድ ቅዱስ ቁርባን ወይንም በእንግሊዘኛው Holy Communion ( ሆሊኮሚኑየን ) መሆኑን እንረዳለን ከዚህም ሌላ መጽሐፍቅዱሳችን እንደሚያስተምረን ከግሪኩ ቃል የተነሳ ምስጋናም የምንሰጥበት ነው በሉቃስ ወንጌል 22 ፥ 17 _ 19 ላይ ጽዋንም ተቀበለ አመስግኖም ይህን እንካችሁ በመካከላችሁም ተካፈሉት እላችኋለሁና፥ የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ ከአሁን ጀምሮ ከወይኑ ፍሬ አልጠጣም አለ እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ ይለናል እንደገናም በ1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 24 _ 25 ላይ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ ይለናል ስለዚህ ቅዱሳን ወገኖች ሳይመሰገን የተሰጠን የጌታ እራት የለምና እኛም ... Read more
Comments
Post a Comment