Seeking Guidance የሚመራ መፈለግ በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ትርፎች በበራችን ላይ በፍጥነት ለእኛ ይገለጣሉ ክፍል ስድስት





Seeking Guidance 



የሚመራ መፈለግ 



በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ትርፎች በበራችን ላይ በፍጥነት ለእኛ ይገለጣሉ


ክፍል ስድስት


የእግዚአብሔር ቃል በመዝሙር 34 8 ላይ እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ  እዩም በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው አለ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለመቅመስ የእግዚአብሔርን ቃል መታዘዝ አማራጭ የሌለው ነገር ነው በ1ኛ ዮሐንስ 3 22 ላይ የእግዚአብሔር ቃል የሚለን እንደዚህ ነው ወዳጆች ሆይ ልባችን ባይፈርድብን በእግዚአብሔር ዘንድ ድፍረት አለን ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን ይለናል በመሆኑም እንግዲህ ለቃሉ በመታዘዝ ውስጥ የሚፈለገው ነገር ሁሉ ከተገኘ በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ትርፎች እንዳሉን በዚሁ በተገለጠው በእግዚአብሔር ቃል መረዳት እንችላለን በትንቢተ ሚልክያስ 3 10 ላይም በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስላችሁ  በዚህ ፈትኑኝ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይለናል እኛ ጌታ በሚያዘን ነገር ሁሉ ታማኞች ሆነን ለቃሉ ከታዘዝን እግዚአብሔር በረከቱን ሁሉ ሊያፈስልን የታመነ ነው ለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስም እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸው መጣሁ ያለው ዮሐንስ ወንጌል 10 10 የሚበዛ ሕይወት ቃሉን ከመታዘዝ የተነሳ በእግዚአብሔር በረከት የተጎበኘና የተጥለቀለቀ ሕይወት ነው ስለዚህም በመዝሙር 111 10 ላይ የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ለሚያደርጓትም ደኅና ማስተዋል አላቸው ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል ይለናልና እግዚአብሔርን ፈርተን የእግዚአብሔርን ቃል በማስተዋል ብናደርግ ማለት ብንታዘዝ  በረከታችንም ሆነ ማስተዋላችን በዚያው ልክ እየጨመረ ይመጣል ጌታ እግዚአብሔር በዚህ በረከት ይባርከን ከዚህ በመቀጠል ከዚሁ ጋር የተያያዘ ጥቂት ሃሳቦችን በእንግሊዝኛ ለማቅረብ እወዳለሁ ይህን የማደርገው ሃሳቡን ይበልጥ ስለሚደግፍልኝና የተሻለ ማብራርያ ስለሚሰጠው ነው 
                  
Obey God's Word AND Prove it right


Put God's word to the test by practicing the things you are learning Acknowledge how his ways bring positive change in your life. The best way to determine that God's commands and teachings bring true peace and blessings is by living them.

God bless all People of God 

God  servant Preacher and Teacher Yonas Asfaw

Comments

Popular posts from this blog

024 ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ነው PART TWO እውነተኛ የምትወደድ ሴት ስትገኝና ኃላፊነት የሚሰማው ባል ሲገኝ ጋብቻ የቤተሰብ መሠረት ይሆናል ምሳሌ 18 ፥ 22 ፤ መዝሙር (128 )፥ 3 _ 4 ጋብቻችን የተበላሸ በሚሆንበት ጊዜ ህብረተሰብን ያልተወሰኑ ሥልጣኔዎችን ግንባታ ያግዳል ማኅበረሰብ ጠንካራ የሚሆነው በጋብቻና በቤተሰብ ውስጥ ነው በባልና በሚስት መካከል የተሻለ መረዳት ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት ሊኖር ይገባል [ የተባረኩ ልጆች ይፈራሉና ] ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ፤ ሮሜ 7 ፥ 2 _ 3 ፤ ኤፌሶን 5 ፥ 25 _ 32 ፤ ኤፌሶን 2 ፥ 19 _ 22 ፤ ሚልክያስ 2 ፥ 15 It was designed to be a lifelong relationship ( Romans 7 : 2 _ 3 ) that would produce godly children ( Malachi 2 : 15 ) በደስታ የሚኖሩ ተጋቢዎች አንዱና ትልቁ የእግዚአብሔር በረከት ተጋቢዎቹ የደስታ ሕይወት ውስጥ መግባታቸው ነው መክብብ 9 ፥ 9 እግዚአብሔር ዲዛይን ያደረገው ጋብቻ ተጋቢዎቹ በደስታ እንዲኖሩ የሚያደርግ ጋብቻ ነው ዘፍጥረት 2 ፥ 24 ሁለት ተጋቢዎች የጋብቻን ቀለበት ሲለዋወጡ የረጅም ጊዜ ቃልኪዳን መግባታቸው ነው A lifelong commitment. Biblically speaking ,this is a covenant a solemn promise to God and one`s mate to be faithful በመጽሐፍቅዱስ አነጋገር የተከበረ ቃልኪዳን የሚባለው ተጋቢዎቹ አንድ ጊዜ ታማኝ የሆኑበት ጉዳይ ነው የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ትምህርቱ በእነዚህ ሃሳቦች ዙርያ የተካተተ በመሆኑ በኦዲዮ የተለቀቁትን ቀጣይና ተከታታይ የሆኑ ትምህርቶች በመስማት እንድትባረኩበት ለእናንተ ለአድማጮች አቅርበነዋል ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

የጌታ እራት ክፍል ሦስት

የመልእክት ርዕስ የሰዎችን ሥራም ሆነ የሥራ ጅማሬን ማወቅ ልታዋርደውም ጀመረች ኃይሉም ከእርሱ ሄደ (መሣፍንት 16 ፥ 9 ) ክፍል አንድ