Seeking Guidance የሚመራ መፈለግ በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ትርፎች በበራችን ላይ በፍጥነት ለእኛ ይገለጣሉ ክፍል ስድስት
Seeking Guidance የሚመራ መፈለግ በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ትርፎች በበራችን ላይ በፍጥነት ለእኛ ይገለጣሉ ክፍል ስድስት የእግዚአብሔር ቃል በመዝሙር 34 ፥ 8 ላይ እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ እዩም በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው አለ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለመቅመስ የእግዚአብሔርን ቃል መታዘዝ አማራጭ የሌለው ነገር ነው በ1ኛ ዮሐንስ 3 ፥ 22 ላይ የእግዚአብሔር ቃል የሚለን እንደዚህ ነው ወዳጆች ሆይ ልባችን ባይፈርድብን በእግዚአብሔር ዘንድ ድፍረት አለን ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን ይለናል በመሆኑም እንግዲህ ለቃሉ በመታዘዝ ውስጥ የሚፈለገው ነገር ሁሉ ከተገኘ በመታዘዝ የሚመጡ ብዙ ትርፎች እንዳሉን በዚሁ በተገለጠው በእግዚአብሔር ቃል መረዳት እንችላለን በትንቢተ ሚልክያስ 3 ፥ 10 ላይም በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይለናል እኛ ጌታ በሚያዘን ነገር ሁሉ ታማኞች ሆነን ለቃሉ ከታዘዝን እግዚአብሔር በረከቱን ሁሉ ሊያፈስልን የታመነ ነው ለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስም እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸው መጣሁ ያለው ዮሐንስ ወንጌል 10 ፥ 10 የሚበዛ ሕይወት ቃሉን ከመታዘዝ የተነሳ በእግዚአብሔር በረከ...