Posts
( ትምህርት አንድ ) የትምህርት ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ……… ዘፍጥረት 17 ፥ 4 _...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ………. ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ የተወደዳችሁ ወገኖች በቅድሚያ የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ በማለት ዛሬ በአዲስ የትምህርት ርዕስ ወደ እናንተ መጥቻለሁ የትምህርቱም ርዕስ እንዲህ የሚል ነው ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ………. ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ በማለት ይናገራል መጽሐፍቅዱሳችን ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ለብዙዎች እንደሚነገር ለዘሮቹም አይልም ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ ይለናል ገላትያ 3 ፥ 16 ታድያ ይህንን ሃሳብ ከዘፍጥረት 17 ፥ 4 _ 8 ከተጻፈው ሃሳብ ጋር በማመሳከር በሰፊው ልንመለከተው እንችላለን ይሁን እንጂ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም ይለናል ገላትያ 3 ፥ 17 ይህ ምን ማለት ነው ስንል ሕግ የመጣው እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቤት አራት መቶ ሠላሳ ዓመቱ ተፈጽሞ በተስፋው ቃል አማካኝነት ተጎብኝተው ከወጡ በኋላ ነው በዘፍጥረት 15 ፥ 12 _ 16 ፣ የሐዋርያት ሥራ 7 ፥ 6 _ 8 በተጻፈው ሃሳብ በአብርሃም በኩል ለእስራኤል የተነገረውን ተስፋ እና ጉብኝቱንም ጭምር እናይበታለን ታድያ የብሉይ ኪዳኑ እስራኤል ከባርነት ቤት ተጎብኝቶ ሲወጣ በተስፋው ቃል ነው እንጂ የወጣው በሕጉ አይደለም ሕጉ በሙሴ በኩል እስራኤል ከባርነት ቤት ከውጡ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የመጣ ነውና እስራኤል ከባርነት ቤት ሊወጡ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን እስኪሽር ድረስ አያፈርስም የሚሽርና የሚያፈርስም አይደለም ይህ ማለት ደግሞ እስራኤል ከባርነት ቤት የወጡት በተስፋው ቃል ነው እንጂ በሕጉ አይደለም ማለትን የሚያሳይ ነው ሙሴም አጥፊው የበኩሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደም መርጨትን በእምነት ካደረገ በኋላ በግብጻውያን በማንኛውም ቤቶች ሞተ በኩር መጣ ለዚህም ነው እንግዲህ ፈርኦንም ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ ከሕዝቤ መካከል ውጡ ሂዱም እንዳላችሁም እግዚአብሔርን አገልግሉ እንዳላችሁም መንጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ውሰዱ ሂዱ እኔንም ደግሞ ባርኩኝ ያላቸው ዘጸአት 12 ፥ 24 _ 32 ፤ ዕብራውያን 11 ፥ 28 ከዚህም ሌላ ሙሉውን ሃሳብ ለማግኘት ዘጸአት 12 ን በሙሉ ማንበብ መልካም ነው ስለዚህ የብሉይ ኪዳኑ እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቤት የወጡት ሕጉ ከመምጣቱ በፊት በነበረውና ለአብርሃምም በተነገረው የተስፋ ቃል ነው ሌላው በተስፋው ቃል ለመውጣታቸው የፈርኦን የራሱ ንግግር በቂ ማስረጃ ነው እንዳላችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ ሂዱ ብሎአልና እስራኤል በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል አስቀድመው የተባሉ ስለሆኑ የግብጽ ንጉስ ፈርኦንም እንዳላችሁም ሂዱ እግዚአብሔርንም አገልግሉ እኔንም ባርኩኝ አላቸው ሌላው ትልቁና ለእኛም አስደናቂ የሆነው ይህ የተስፋ ቃል አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳን ያለበት የተስፋ ቃል ስለሆነ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ወይንም የመጣው ሕግ የማይሽረውና የማያፈርሰው መሆኑ ነው በመሆኑም በብሉይ ከዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ሰዎች ከባርነት ቤት የሚፈቱትና ነጻ የሚወጡት አስቀድሞ በተረጋገጠው ኪዳንና የተስፋ ቃል ነው ታድያ ይህንኑ የተስፋ ቃል ነው ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ለብዙዎች እንደሚነገር ለዘሮቹም አይልም ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ በማለት ሐዋርያው የነገረን በመሆኑም በዚህ አስቀድሞ በእግዚአብሔር በተረጋገጠው ኪዳንና የተስፋ ቃላችን በሆነው በክርስቶስ ዛሬ ላይ በሐዲስ ኪዳን ያለን ሕዝቦች ከባርነት ቤትና ከሰይጣን እስራት ከጨለማውም ግዛት በዚሁ በክርስቶስ ለአንዴና ለዘላለም ተፈተናል ከዚሁ ባርነትም ተላቀናል ፣ ወጥተናል የብሉይ ኪዳን እስራኤል ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ ነው ከግብጽ የባርነት ቤት በሕጉ ሳይሆን በዚሁ የተስፋ ቃል የወጡት አጥፊው የበኩሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨት ያደረገላቸው ሙሴ ነው ለእኛ በሐዲስ ኪዳን ላይ ላለን ሕዝቦች ግን ፋሲካችን የሆነና ደሙንም በእኛ ላይ በመርጨት ከባርነት ቤት ከሰይጣንም ግዞት ለዘላለም ያወጣን ክርስቶስ ነው ለዚህም ነው ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾ አይደለም ሲል ሐዋርያው የነገረን 2ኛ ቆሮንቶስ 5 ፥ 6 _ 8 ወገኖቼ ታድያ አሁን ከቃሉ እንደተማርነው በዚህ ጌታ በናዝሬቱ ኢየሱስ መዳን አሁን የመጣ ትምህርት ወይም ዛሬ የተገኘ አለበለዚያም ብዙዎች እንደሚሉት ከሌሎች የተኮረጀ ወይም መጤ የሆነ ሳይሆን አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳንና የተስፋ ቃል የሆነ ነው በመሆኑም ሊያድነን አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳንና የተስፋ ቃል የሆነንን ኢየሱስን የሚሽር የትኛውም ሕግ የለም ስለዚህ የምንድነው አስቀድሞ በእግዚአብሔር በተረጋገጠው ኪዳናችንና የተስፋም ቃላችን በሆነው በኢየሱስ ብቻ ነው ኢየሱስ አንድና ብቸኛ የሆነ የመዳኛ መንገዳችን ነው ከዚህ ውጪ ሌላ የመዳኛ መንገድ የለም የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ አስቀድሞ በእግዚአብሔር በተረጋገጠው ኪዳናችንና ተስፋችን በሆነው በኢየሱስ ብቻ መዳን እንዳለ የሚጠቁም ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ወይም የመጣው ሕግ የሰው ልጆችን ሕያው ሊያደርግ የሚችል አለመሆኑንና ጽድቅም በሕግ በኩል እንዳልሆነ ያመላክታል እንደገናም ይኸው ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የመጣው ሕግ የሰው ልጆችን የሚያድን ካለመሆኑም የተነሳ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚቃወም አለመሆኑንም ይጠቁመናል በመሆኑም ዛሬ በሐዲስ ኪዳን ሰዎች የሕግን ማንነትና ምንነት በትክክል ተረድተው ሊያድናቸው ወደሚችል የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ማለትም ወደ ክርስቶስ ያለጥርጥር በእርግጠኝነት ሊመጡ ይገባል ወገኖች እንግዲህ ትምህርቱ እነዚህንና የመሣሠሉትን ሁሉ በሰፊው ያብራራል ስለሆነም ከዚህ በመቀጠል በየተራ የሚለቀቁትን ቪዲዮዎች እየተከታተላችሁ በመስማት ለሌሎችም ሰዎች ሼር እንድታደርጉት ስል ከትልቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ተባረኩልኝ የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
- Get link
- X
- Other Apps
( ትምህርት አንድ ) የትምህርት ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ……… ዘፍጥረት 17 ፥ 4 _...
- Get link
- X
- Other Apps
( ትምህርት አንድ ) የትምህርት ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ……… ዘፍጥረት 17 ፥ 4 ...የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርቱ ርዕስ ፦ ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ………. ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ የተወደዳችሁ ወገኖች በቅድሚያ የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ በማለት ዛሬ በአዲስ የትምህርት ርዕስ ወደ እናንተ መጥቻለሁ የትምህርቱም ርዕስ እንዲህ የሚል ነው ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ………. ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ በማለት ይናገራል መጽሐፍቅዱሳችን ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ለብዙዎች እንደሚነገር ለዘሮቹም አይልም ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ ይለናል ገላትያ 3 ፥ 16 ታድያ ይህንን ሃሳብ ከዘፍጥረት 17 ፥ 4 _ 8 ከተጻፈው ሃሳብ ጋር በማመሳከር በሰፊው ልንመለከተው እንችላለን ይሁን እንጂ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን የተስፋውን ቃል እስኪሽር ድረስ አያፈርስም ይለናል ገላትያ 3 ፥ 17 ይህ ምን ማለት ነው ስንል ሕግ የመጣው እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቤት አራት መቶ ሠላሳ ዓመቱ ተፈጽሞ በተስፋው ቃል አማካኝነት ተጎብኝተው ከወጡ በኋላ ነው በዘፍጥረት 15 ፥ 12 _ 16 ፣ የሐዋርያት ሥራ 7 ፥ 6 _ 8 በተጻፈው ሃሳብ በአብርሃም በኩል ለእስራኤል የተነገረውን ተስፋ እና ጉብኝቱንም ጭምር እናይበታለን ታድያ የብሉይ ኪዳኑ እስራኤል ከባርነት ቤት ተጎብኝቶ ሲወጣ በተስፋው ቃል ነው እንጂ የወጣው በሕጉ አይደለም ሕጉ በሙሴ በኩል እስራኤል ከባርነት ቤት ከውጡ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የመጣ ነውና እስራኤል ከባርነት ቤት ሊወጡ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠውን ኪዳን እስኪሽር ድረስ አያፈርስም የሚሽርና የሚያፈርስም አይደለም ይህ ማለት ደግሞ እስራኤል ከባርነት ቤት የወጡት በተስፋው ቃል ነው እንጂ በሕጉ አይደለም ማለትን የሚያሳይ ነው ሙሴም አጥፊው የበኩሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደም መርጨትን በእምነት ካደረገ በኋላ በግብጻውያን በማንኛውም ቤቶች ሞተ በኩር መጣ ለዚህም ነው እንግዲህ ፈርኦንም ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ ከሕዝቤ መካከል ውጡ ሂዱም እንዳላችሁም እግዚአብሔርን አገልግሉ እንዳላችሁም መንጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ውሰዱ ሂዱ እኔንም ደግሞ ባርኩኝ ያላቸው ዘጸአት 12 ፥ 24 _ 32 ፤ ዕብራውያን 11 ፥ 28 ከዚህም ሌላ ሙሉውን ሃሳብ ለማግኘት ዘጸአት 12 ን በሙሉ ማንበብ መልካም ነው ስለዚህ የብሉይ ኪዳኑ እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቤት የወጡት ሕጉ ከመምጣቱ በፊት በነበረውና ለአብርሃምም በተነገረው የተስፋ ቃል ነው ሌላው በተስፋው ቃል ለመውጣታቸው የፈርኦን የራሱ ንግግር በቂ ማስረጃ ነው እንዳላችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ ሂዱ ብሎአልና እስራኤል በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል አስቀድመው የተባሉ ስለሆኑ የግብጽ ንጉስ ፈርኦንም እንዳላችሁም ሂዱ እግዚአብሔርንም አገልግሉ እኔንም ባርኩኝ አላቸው ሌላው ትልቁና ለእኛም አስደናቂ የሆነው ይህ የተስፋ ቃል አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳን ያለበት የተስፋ ቃል ስለሆነ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ወይንም የመጣው ሕግ የማይሽረውና የማያፈርሰው መሆኑ ነው በመሆኑም በብሉይ ከዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ሰዎች ከባርነት ቤት የሚፈቱትና ነጻ የሚወጡት አስቀድሞ በተረጋገጠው ኪዳንና የተስፋ ቃል ነው ታድያ ይህንኑ የተስፋ ቃል ነው ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ ለብዙዎች እንደሚነገር ለዘሮቹም አይልም ለአንድ እንደሚነገር ግን ለዘርህም ይላል እርሱም ክርስቶስ በማለት ሐዋርያው የነገረን በመሆኑም በዚህ አስቀድሞ በእግዚአብሔር በተረጋገጠው ኪዳንና የተስፋ ቃላችን በሆነው በክርስቶስ ዛሬ ላይ በሐዲስ ኪዳን ያለን ሕዝቦች ከባርነት ቤትና ከሰይጣን እስራት ከጨለማውም ግዛት በዚሁ በክርስቶስ ለአንዴና ለዘላለም ተፈተናል ከዚሁ ባርነትም ተላቀናል ፣ ወጥተናል የብሉይ ኪዳን እስራኤል ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ ነው ከግብጽ የባርነት ቤት በሕጉ ሳይሆን በዚሁ የተስፋ ቃል የወጡት አጥፊው የበኩሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨት ያደረገላቸው ሙሴ ነው ለእኛ በሐዲስ ኪዳን ላይ ላለን ሕዝቦች ግን ፋሲካችን የሆነና ደሙንም በእኛ ላይ በመርጨት ከባርነት ቤት ከሰይጣንም ግዞት ለዘላለም ያወጣን ክርስቶስ ነው ለዚህም ነው ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾ አይደለም ሲል ሐዋርያው የነገረን 2ኛ ቆሮንቶስ 5 ፥ 6 _ 8 ወገኖቼ ታድያ አሁን ከቃሉ እንደተማርነው በዚህ ጌታ በናዝሬቱ ኢየሱስ መዳን አሁን የመጣ ትምህርት ወይም ዛሬ የተገኘ አለበለዚያም ብዙዎች እንደሚሉት ከሌሎች የተኮረጀ ወይም መጤ የሆነ ሳይሆን አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳንና የተስፋ ቃል የሆነ ነው በመሆኑም ሊያድነን አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠ ኪዳንና የተስፋ ቃል የሆነንን ኢየሱስን የሚሽር የትኛውም ሕግ የለም ስለዚህ የምንድነው አስቀድሞ በእግዚአብሔር በተረጋገጠው ኪዳናችንና የተስፋም ቃላችን በሆነው በኢየሱስ ብቻ ነው ኢየሱስ አንድና ብቸኛ የሆነ የመዳኛ መንገዳችን ነው ከዚህ ውጪ ሌላ የመዳኛ መንገድ የለም የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ አስቀድሞ በእግዚአብሔር በተረጋገጠው ኪዳናችንና ተስፋችን በሆነው በኢየሱስ ብቻ መዳን እንዳለ የሚጠቁም ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ወይም የመጣው ሕግ የሰው ልጆችን ሕያው ሊያደርግ የሚችል አለመሆኑንና ጽድቅም በሕግ በኩል እንዳልሆነ ያመላክታል እንደገናም ይኸው ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የመጣው ሕግ የሰው ልጆችን የሚያድን ካለመሆኑም የተነሳ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል የሚቃወም አለመሆኑንም ይጠቁመናል በመሆኑም ዛሬ በሐዲስ ኪዳን ሰዎች የሕግን ማንነትና ምንነት በትክክል ተረድተው ሊያድናቸው ወደሚችል የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ማለትም ወደ ክርስቶስ ያለጥርጥር በእርግጠኝነት ሊመጡ ይገባል ወገኖች እንግዲህ ትምህርቱ እነዚህንና የመሣሠሉትን ሁሉ በሰፊው ያብራራል ስለሆነም ከዚህ በመቀጠል በየተራ የሚለቀቁትን ቪዲዮዎች እየተከታተላችሁ በመስማት ለሌሎችም ሰዎች ሼር እንድታደርጉት ስል ከትልቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ተባረኩልኝ የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
- Get link
- X
- Other Apps
ትምህርት ሁለት እግዚአብሔር የማጣርያ ጊዜ አለው የትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች በዚህ የትምህርት ሁለት ክፍለ ጊዜ የምንመለከተው በዳዊትና በኦርዮ ቤት መካከል እግዚአብሔር ያደረገውን ማጣርያ ነው በዚህ ውስጥ ለማጣርያነት የተጠቀመበት ነቢዩ ናታንን ነው ስለዚህም ነቢዩ ናታን ጥበብ በተሞላበት የምሳሌ ቃል ወደ ዳዊት ከቀረበ በኋላ ዳዊት በገዛ አንደበቱ ተቆጥቶ እንዲህ ያደረገ ሰው ሞት ይገባዋል በማለት ፍርድ ሰጠ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ነቢዩ ናታን ያለምንም ማንገራገርና ማመንታት ያ ሰው አንተ ነህ ያለው ከዚያ በኋላም አቃለኸኛልና የኬጢያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሖን ዘንድ ወስደሃልና ከቤትሕ ሰይፍ አይርቅም አለው ወገኖቼ እግዚአብሔር ጣልቃ ሲገባ ሰዎች ምንም ዓይነት ሰዎች ይሁኑ ራሳቸውን መደበቅም ይሁን ከራሳቸው መደበቅ አይችሉም የእግዚአብሔር ማጣርያ ካሉበት ነገር ውስጥ ፈልፍሎ ያወጣቸዋል ለዚህ የሚበጀው ነገር ወይም መፍትሔው ታድያ በእግዚአብሔር ማጣርያ ውስጥ ገብተው ሳይቀሉ ወይንም ያ ሰው አንተ ነህ ሳይባሉ ቶሎ በጊዜ ራስን ከተደበቁበት ወይም ከደበቁበት ነገር አወጥቶ ያ ሰው እኔ ነኝ በማለት ለንስሐና በሕይወት ለሚመጣ ለውጥ ይህንኑ ማንነት አሳልፎ መስጠት አዋቂነት ነው ሐዋርያው ጳውሎስ ማንም ሳይለው በሰዎች በኩልም ኃጢአተኛውና አሳዳጁ አንተ ነህ ሳይባል ከኃጢአተኞችም ዋናው እኔ ነኝ አለ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁ ምሕረትን አገኘሁ በማለት ተናገረ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1 ፥ 13 ታድያ አንዳንድ ጊዜ በሰራነው በደል አንተ ነህ እስክንባል መጠበቅ የለብንም ጥፋት እንደሰራን ገብቶን ከሆነ ማለት ያለብን እንደ ጳውሎስ ከኃጢአተኞችም ዋናው እኔ ነኝ ነው ያኔ ጌታ እግዚአብሔር መሐሪ አምላክ ስለሆነ የትኛውንም የተላለፍንበትን ኃጢአት ይቅር ይላል ሁለተኛው ሃሳብ በመርዶክዮስና በሐማ መካከል እግዚአብሔር የሕይወት ማጣርያ ሊያደርግ የተጠቀመበት መንገድ ነው መጠቀምያም ያደረጋት ለንግስትነት የቀረበችውን አስቴርን ነው አስቴር ግብዣ አድርጋ ንጉስ አርጤቅሲስንና ሐማን ወደ ግብዣ ከጠራች በኋላ ሐማ ባለ ማስተዋል አንድ ነገር ተናገረ ንግሥቲቱ ወዳዘጋጀችው ግብዣ ከእኔ በቀር ማንንም አልጠራችም ደግሞ ነገ ከንጉሡ ጋር ወደ እርስዋ ተጠርቻለሁ ነገር ግን አይሁዳዊ መርዶክዮስ በንጉሡ በር ተቀምጦ ካየሁ ይህ ሁሉ ለእኔ ምንም አይጠቅምም አለ ከዚያ በኋላ ነው በዘመዶቹ አነሳሽነት መርዶክዮስን ለማስገደል ግንዱን አስደረገ የሚለን ይህ እንግዲህ የሐማ ትልቁ ሞኝነት እና አላዋቂነቱ ነው ግብዣዎች ሁሉ አንዳንድ ጊዜ መልካም ናቸው ልንል ብንችልም ነገር ግን እግዚአብሔር በአስቴር በኩል ለንጉስ አርጤቅሲስና ለሐማ ያዘጋጀው ግብዣ የሐማን ማንነት ከመርዶክዮስ ይልቅ ለይቶ ለማወቅ የተዘጋጀ የእግዚአብሔር የማጣርያ ግብዣ ነው መጽሐፈ አስቴር 5 ፥ 12 _ ፍጻሜ ፣ መጽሐፈ አስቴር ምዕራፍ 6 ፣ ምዕራፍ 7 በሙሉ እናንብብ ታድያ በዚህ ግብዣ ላይ ሐማ እንዳለውና እንደፎከረው ተደስቶ ወይም ጥቅም አግኝቶ ግብዣው የተጠናቀቀ አይደለም ግብዣው የተጠናቀቀው ወይም የተደመደመው ሐማ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ እንዲሰቀል ተበይኖ ፣ ሐማም ተሰቅሎ ፣ የንጉሡም ቁጣ ከሐማ መሰቀል የተነሳ በርዶ ነው አንዳንድ ግብዣዎች እንግዲህ ሐማ እንደጠበቃቸው ዓይነት ግብዣዎች ሳይሆኑ ቀርተው እና በምትኩም የእግዚአብሔርን ጽኑ የሕይወት ማጣርያን አምጥተው ይጠናቀቃሉ ለዚህም ነው መጽሐፍቅዱሳችን ሐማንም ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሰቀሉት በዚያም ጊዜ የንጉሡ ቁጣ በረደ ሲል የዘገበልን ከዚህም ሌላ ሐማ ለራሱ ባሰበው ፈረስ መርዶክዮስን ያስቀመጠ ፣ ለራሱ ያሰበውን ዘውድ ለመርዶክዮስ የጫነ ለራሱ ያሰበውን ልብሰ መንግሥት መርዶክዮስን ያለበሰ በአንጻሩ ደግሞ ለመርዶክዮስ ሞት ባዘጋጀው ግንድ ራሱ የተሰቀለ ነበረ የእግዚአብሔር የማጣርያ ጊዜ ሲመጣ እንግዲህ ዛሬም እንዲሁ ነው ከእኔ ወዲያ ስንል ለራሳችን ያመቻቸነው ለሌሎች ይሆናል ለነገሌ መጥፊያ ይሆናል ስንል ያወሳሰብነው ራሳችንን ያጠፋል ስለዚህ እግዚአብሔር ከዚህ የተሳሳተ ክፉ ሥራ እና እኩይ ተግባር ይጠብቀን የተወደዳችሁ ቅዱሳን የትምህርት ሁለት ሃሳብ በጣም ሰፊ ነው ነገር ግን ከዚህ ሌላ በውስጡ በቪዲዮ የተለቀቁ ብዙ የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች ያሉበት ማብራርያዎች አሉ እና በመቀጠል እንደሚከተለው በዚሁ ቪዲዮ የተለቀቁትን መልዕክቶች እየገባችሁ በመስማት ይበልጥ በስፋት መከታተል የምትችሉ መሆናችሁን በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን
- Get link
- X
- Other Apps
ትምህርት ሁለት ፦ እግዚአብሔር የማጣርያ ጊዜ አለው 2ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 11 እና ምዕራፍ 12 በሙሉ ፤ መዝሙር 1..ትምህርት ሁለት እግዚአብሔር የማጣርያ ጊዜ አለው የትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች በዚህ የትምህርት ሁለት ክፍለ ጊዜ የምንመለከተው በዳዊትና በኦርዮ ቤት መካከል እግዚአብሔር ያደረገውን ማጣርያ ነው በዚህ ውስጥ ለማጣርያነት የተጠቀመበት ነቢዩ ናታንን ነው ስለዚህም ነቢዩ ናታን ጥበብ በተሞላበት የምሳሌ ቃል ወደ ዳዊት ከቀረበ በኋላ ዳዊት በገዛ አንደበቱ ተቆጥቶ እንዲህ ያደረገ ሰው ሞት ይገባዋል በማለት ፍርድ ሰጠ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ነቢዩ ናታን ያለምንም ማንገራገርና ማመንታት ያ ሰው አንተ ነህ ያለው ከዚያ በኋላም አቃለኸኛልና የኬጢያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሖን ዘንድ ወስደሃልና ከቤትሕ ሰይፍ አይርቅም አለው ወገኖቼ እግዚአብሔር ጣልቃ ሲገባ ሰዎች ምንም ዓይነት ሰዎች ይሁኑ ራሳቸውን መደበቅም ይሁን ከራሳቸው መደበቅ አይችሉም የእግዚአብሔር ማጣርያ ካሉበት ነገር ውስጥ ፈልፍሎ ያወጣቸዋል ለዚህ የሚበጀው ነገር ወይም መፍትሔው ታድያ በእግዚአብሔር ማጣርያ ውስጥ ገብተው ሳይቀሉ ወይንም ያ ሰው አንተ ነህ ሳይባሉ ቶሎ በጊዜ ራስን ከተደበቁበት ወይም ከደበቁበት ነገር አወጥቶ ያ ሰው እኔ ነኝ በማለት ለንስሐና በሕይወት ለሚመጣ ለውጥ ይህንኑ ማንነት አሳልፎ መስጠት አዋቂነት ነው ሐዋርያው ጳውሎስ ማንም ሳይለው በሰዎች በኩልም ኃጢአተኛውና አሳዳጁ አንተ ነህ ሳይባል ከኃጢአተኞችም ዋናው እኔ ነኝ አለ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁ ምሕረትን አገኘሁ በማለት ተናገረ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1 ፥ 13 ታድያ አንዳንድ ጊዜ በሰራነው በደል አንተ ነህ እስክንባል መጠበቅ የለብንም ጥፋት እንደሰራን ገብቶን ከሆነ ማለት ያለብን እንደ ጳውሎስ ከኃጢአተኞችም ዋናው እኔ ነኝ ነው ያኔ ጌታ እግዚአብሔር መሐሪ አምላክ ስለሆነ የትኛውንም የተላለፍንበትን ኃጢአት ይቅር ይላል ሁለተኛው ሃሳብ በመርዶክዮስና በሐማ መካከል እግዚአብሔር የሕይወት ማጣርያ ሊያደርግ የተጠቀመበት መንገድ ነው መጠቀምያም ያደረጋት ለንግስትነት የቀረበችውን አስቴርን ነው አስቴር ግብዣ አድርጋ ንጉስ አርጤቅሲስንና ሐማን ወደ ግብዣ ከጠራች በኋላ ሐማ ባለ ማስተዋል አንድ ነገር ተናገረ ንግሥቲቱ ወዳዘጋጀችው ግብዣ ከእኔ በቀር ማንንም አልጠራችም ደግሞ ነገ ከንጉሡ ጋር ወደ እርስዋ ተጠርቻለሁ ነገር ግን አይሁዳዊ መርዶክዮስ በንጉሡ በር ተቀምጦ ካየሁ ይህ ሁሉ ለእኔ ምንም አይጠቅምም አለ ከዚያ በኋላ ነው በዘመዶቹ አነሳሽነት መርዶክዮስን ለማስገደል ግንዱን አስደረገ የሚለን ይህ እንግዲህ የሐማ ትልቁ ሞኝነት እና አላዋቂነቱ ነው ግብዣዎች ሁሉ አንዳንድ ጊዜ መልካም ናቸው ልንል ብንችልም ነገር ግን እግዚአብሔር በአስቴር በኩል ለንጉስ አርጤቅሲስና ለሐማ ያዘጋጀው ግብዣ የሐማን ማንነት ከመርዶክዮስ ይልቅ ለይቶ ለማወቅ የተዘጋጀ የእግዚአብሔር የማጣርያ ግብዣ ነው መጽሐፈ አስቴር 5 ፥ 12 _ ፍጻሜ ፣ መጽሐፈ አስቴር ምዕራፍ 6 ፣ ምዕራፍ 7 በሙሉ እናንብብ ታድያ በዚህ ግብዣ ላይ ሐማ እንዳለውና እንደፎከረው ተደስቶ ወይም ጥቅም አግኝቶ ግብዣው የተጠናቀቀ አይደለም ግብዣው የተጠናቀቀው ወይም የተደመደመው ሐማ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ እንዲሰቀል ተበይኖ ፣ ሐማም ተሰቅሎ ፣ የንጉሡም ቁጣ ከሐማ መሰቀል የተነሳ በርዶ ነው አንዳንድ ግብዣዎች እንግዲህ ሐማ እንደጠበቃቸው ዓይነት ግብዣዎች ሳይሆኑ ቀርተው እና በምትኩም የእግዚአብሔርን ጽኑ የሕይወት ማጣርያን አምጥተው ይጠናቀቃሉ ለዚህም ነው መጽሐፍቅዱሳችን ሐማንም ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሰቀሉት በዚያም ጊዜ የንጉሡ ቁጣ በረደ ሲል የዘገበልን ከዚህም ሌላ ሐማ ለራሱ ባሰበው ፈረስ መርዶክዮስን ያስቀመጠ ፣ ለራሱ ያሰበውን ዘውድ ለመርዶክዮስ የጫነ ለራሱ ያሰበውን ልብሰ መንግሥት መርዶክዮስን ያለበሰ በአንጻሩ ደግሞ ለመርዶክዮስ ሞት ባዘጋጀው ግንድ ራሱ የተሰቀለ ነበረ የእግዚአብሔር የማጣርያ ጊዜ ሲመጣ እንግዲህ ዛሬም እንዲሁ ነው ከእኔ ወዲያ ስንል ለራሳችን ያመቻቸነው ለሌሎች ይሆናል ለነገሌ መጥፊያ ይሆናል ስንል ያወሳሰብነው ራሳችንን ያጠፋል ስለዚህ እግዚአብሔር ከዚህ የተሳሳተ ክፉ ሥራ እና እኩይ ተግባር ይጠብቀን የተወደዳችሁ ቅዱሳን የትምህርት ሁለት ሃሳብ በጣም ሰፊ ነው ነገር ግን ከዚህ ሌላ በውስጡ በቪዲዮ የተለቀቁ ብዙ የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች ያሉበት ማብራርያዎች አሉ እና በመቀጠል እንደሚከተለው በዚሁ ቪዲዮ የተለቀቁትን መልዕክቶች እየገባችሁ በመስማት ይበልጥ በስፋት መከታተል የምትችሉ መሆናችሁን በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን.