Posts
Showing posts from November, 2015
M2U00052 የትምህርት ርዕስ ጉዳዩ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሆነ ሰው ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በተላለፉ ጊዜ መልዕክት አለው ሙሴም አለ፦ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ ? አይጠቅማችሁም እግዚአብሔር በእናንተ መካከል አይደለምና በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትወድቁ አትውጡ ዘኊልቊ 14 ፥ 41 ፣ 39 _ 45 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ ትምህርት በጌታ አማኞች ለሆኑ ቅዱሳንና የጌታ አገልጋዮች በሙሉ እየተላለፈ ያለ ትምህርት ነው ይሁን እንጂ ለእግዚአብሔር ቃል የተከፈተ ልብ አለኝ ማደግ መማር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለሕይወቴ አውቄ ለጌታ መታዘዝና ጌታን ማክበር እፈልጋለሁ የሚል ክርስቲያን ሁሉ ሊማረው ሊከታተለውና ሊጠቀምበት ይችላል ትምህርቱ ተከታታይነትና ቀጣይነት ያለው ትምህርት በመሆኑ መነሻ አለው ለዚህ ለዛሬው የትምህርት አቅርቦት እንደ መነሻ የሆነውን ትምህርት ባለፈው ጊዜ በተከታታይ በቪዲዮ የለቀኩት በመሆኑ ጉዳያችን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ይሁን በሚል የትምህርት አርዕስት ዘኊልቊ 9 ፥ 18 ፤ ዘኊልቊ 9 ፥ 23 ላይ የተጠቀሱትን ሃሳቦች መነሻ ሃሳብ አድርገን ጉዳያቸው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ የሆነ እስራኤል በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይጓዙ ነበር በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር በሙሴም እጅ እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ይጠብቁ ነበር በማለት ከዚህ የተነሳ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ጉዳይ የሙሴም ሆነ የእግዚአብሔር ብቸኛ ጉዳይ ሳይሆን የእስራኤልም ጉዳይ በመሆኑ ምንም እንኳ በሙሴ እጅ እንዳዘዘው ቢሆንም እስራኤል ግን ጉዳያቸው ሙሴ ሳይሆን የእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር የሚለውን ሃሳብ አንስተን በስፋት መማማራችን ይታወሳል ከዚሁም ጋራ ሌሎችንም ቅዱሳን ሰዎችን ከመጽሐፍቅዱሳችን በማንሳት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጉዳያቸው በማድረጋቸው ምክንያት ያገኙትን ጠቀሜታ ሰፋ ባለ ሁኔታ እያብራራን ተማምረንበታል ቪዲዮዎቹ በፌስቡኬም ሆነ በዌብሳይቴ ወይም በዩቲዩብ የተለቀቁ በመሆናቸው እየገባችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናችሁን ለማሳሰብ እወዳለሁ ዌብሳይቴምwww.Joshua.yonasgetaneh.com ነው የተከታተላችሁ ትምህርቱንም የሰማችሁ ቅዱሳን ደግሞ ይህ ትምህርት ለዛሬው ትምህርቴ እንደ መንደርደርያና መነሻ ሃሳብ የሚሆን ስለሆነ ትምህርቱ ተያያዥነት ያለው ነውና እንዲያያዝላችሁ የዛሬው ትምህርትም ይበልጥ ግልጽ እንዲሆንላችሁ እንዲህ ስል አቅርቤዋለሁ ጉዳዩ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሆነ ሰው በቃ ጉዳዬ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው ሲል እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በተላለፉ ጊዜ እንደ ሙሴ ብድግ ብሎ ስለምን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ትተላለፋላችሁ ? አይጠቅማችሁም እግዚአብሔር በእናንተ መካከል አይደለምና በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትወድቁ አትውጡ ይላል እንዲህ ዓይነቱ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመተላለፍ ጉዳይ ይሉኝታ አያጠቃውም ዛሬ ቢተላለፉም ቆይ ነገና ተነገ ወዲያ ይጠብቁ ይሆናል አለበለዚያም አንድ ቀን ይጠብቃሉ በቃ የሚል ድምጽም የለውም ማስተላለፍ የሚገባውን መልዕክት ያስተላልፋል አድርግ ፈጽም የተባለውን ያደርጋል ይፈጽማል ውጤቱን ግን ለእግዚአብሔር ይተዋል የሚለውንና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ደግሞ ጥቅሙ ለሁላችንም ነው የሚሉትን አንኳር ሃሳቦች ያካተተ በመሆኑ ትምህርቱ በዚህ ዙርያ ያጠነጠነ ነው ትምህርቱ የሚቀጥልና ያላለቀ በመሆኑም ቀጣይ መልዕክት አለው ስለዚህ ቅዱሳን የተለቀቀውን ትምህርት ስሙት ተባረኩበት ለሌሎችም ሊሰሙ ለሚችሉ አስተላልፉት ሼር አድርጉት ስል በአክብሮት ለማሳሰብ እወዳለሁ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
- Get link
- X
- Other Apps
M2U00051 የትምህርት ርዕስ ጉዳዩ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሆነ ሰው ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በተላለፉ ጊዜ መልዕክት አለው ሙሴም አለ፦ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ ? አይጠቅማችሁም እግዚአብሔር በእናንተ መካከል አይደለምና በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትወድቁ አትውጡ ዘኊልቊ 14 ፥ 41 ፣ 39 _ 45 የተወደዳችሁ ቅዱሳን ይህ ትምህርት በጌታ አማኞች ለሆኑ ቅዱሳንና የጌታ አገልጋዮች በሙሉ እየተላለፈ ያለ ትምህርት ነው ይሁን እንጂ ለእግዚአብሔር ቃል የተከፈተ ልብ አለኝ ማደግ መማር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለሕይወቴ አውቄ ለጌታ መታዘዝና ጌታን ማክበር እፈልጋለሁ የሚል ክርስቲያን ሁሉ ሊማረው ሊከታተለውና ሊጠቀምበት ይችላል ትምህርቱ ተከታታይነትና ቀጣይነት ያለው ትምህርት በመሆኑ መነሻ አለው ለዚህ ለዛሬው የትምህርት አቅርቦት እንደ መነሻ የሆነውን ትምህርት ባለፈው ጊዜ በተከታታይ በቪዲዮ የለቀኩት በመሆኑ ጉዳያችን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ይሁን በሚል የትምህርት አርዕስት ዘኊልቊ 9 ፥ 18 ፤ ዘኊልቊ 9 ፥ 23 ላይ የተጠቀሱትን ሃሳቦች መነሻ ሃሳብ አድርገን ጉዳያቸው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ የሆነ እስራኤል በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይጓዙ ነበር በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር በሙሴም እጅ እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ይጠብቁ ነበር በማለት ከዚህ የተነሳ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ጉዳይ የሙሴም ሆነ የእግዚአብሔር ብቸኛ ጉዳይ ሳይሆን የእስራኤልም ጉዳይ በመሆኑ ምንም እንኳ በሙሴ እጅ እንዳዘዘው ቢሆንም እስራኤል ግን ጉዳያቸው ሙሴ ሳይሆን የእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር የሚለውን ሃሳብ አንስተን በስፋት መማማራችን ይታወሳል ከዚሁም ጋራ ሌሎችንም ቅዱሳን ሰዎችን ከመጽሐፍቅዱሳችን በማንሳት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጉዳያቸው በማድረጋቸው ምክንያት ያገኙትን ጠቀሜታ ሰፋ ባለ ሁኔታ እያብራራን ተማምረንበታል ቪዲዮዎቹ በፌስቡኬም ሆነ በዌብሳይቴ ወይም በዩቲዩብ የተለቀቁ በመሆናቸው እየገባችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናችሁን ለማሳሰብ እወዳለሁ ዌብሳይቴምwww.Joshua.yonasgetaneh.com ነው የተከታተላችሁ ትምህርቱንም የሰማችሁ ቅዱሳን ደግሞ ይህ ትምህርት ለዛሬው ትምህርቴ እንደ መንደርደርያና መነሻ ሃሳብ የሚሆን ስለሆነ ትምህርቱ ተያያዥነት ያለው ነውና እንዲያያዝላችሁ የዛሬው ትምህርትም ይበልጥ ግልጽ እንዲሆንላችሁ እንዲህ ስል አቅርቤዋለሁ ጉዳዩ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሆነ ሰው በቃ ጉዳዬ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው ሲል እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በተላለፉ ጊዜ እንደ ሙሴ ብድግ ብሎ ስለምን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ትተላለፋላችሁ ? አይጠቅማችሁም እግዚአብሔር በእናንተ መካከል አይደለምና በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትወድቁ አትውጡ ይላል እንዲህ ዓይነቱ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመተላለፍ ጉዳይ ይሉኝታ አያጠቃውም ዛሬ ቢተላለፉም ቆይ ነገና ተነገ ወዲያ ይጠብቁ ይሆናል አለበለዚያም አንድ ቀን ይጠብቃሉ በቃ የሚል ድምጽም የለውም ማስተላለፍ የሚገባውን መልዕክት ያስተላልፋል አድርግ ፈጽም የተባለውን ያደርጋል ይፈጽማል ሌላውን ግን ለእግዚአብሔር ይተዋል የሚለውንና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ደግሞ ጥቅሙ ለሁላችንም ነው የሚሉትን አንኳር ሃሳቦች ያካተተ በመሆኑ ትምህርቱ በዚህ ዙርያ ያጠነጠነ ነው ትምህርቱ የሚቀጥልና ያላለቀ በመሆኑም ቀጣይ መልዕክት አለው ስለዚህ ቅዱሳን የተለቀቀውን ትምህርት ስሙት ተባረኩበት ሌሎችም ሊሰሙ ለሚችሉ አስተላልፉት ሼር አድርጉት ስል በአክብሮት ለማሳሰብ እወዳለሁ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
- Get link
- X
- Other Apps
ማዕበል የማይቀርበው መርከባችን
- Get link
- X
- Other Apps
የትምህርት ርዕስ ሐመርነ ዘኢይቀርቦ ሞገድ ማዕበል የማይቀርበው መርከባችን ንዑስ አርዕስት ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውሃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ ………… ክፍል ሦስት በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ሐመርነ ዘኢይቀርቦ ሞገድ መዝገብነ ዘኢይረክቦ ሰራቂ ወኢያማስኖ ፃፄ ወቊንቊኔ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ትርጉም ፦ ማዕበል የማይቀርበው መርከባችን ሌባ የማያገኘው ብል ነቀዝ የማያበላሸው ሳጥናችን ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ( ምንጭ መጽሐፈ ሰዓታት ) የተወደዳችሁ አባቶች ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና የእግዚአብሔር ሕዝብ ምዕመናን በሙሉ የእግዚአብሔር...