የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ? ለዛሬ ያለው ትርጉም Meaning for today ክፍል ዘጠኝ
የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ? ለዛሬ ያለው ትርጉም Meaning for today ክፍል ዘጠኝ ዛሬን ስንጠይቅ ለክርስቲያኑ የጌታ እራት ትርጉሙ እንዴት ነው ? ሦስት የተያያዙ ሃሳቦች ለሃላፊ ጊዜ ፣ ለአሁን ጊዜና ለወደፊት ጊዜ ሊጠቅሙ የሚችሉ ሲሆኑ እነርሱም ተያይዘው ያሉና የተገናኙም ናቸው 1ኛ ) የጌታ እራት የጌታን መታሰቢያ ጊዜ የምናስታውስበት ነው ጌታም እንዲህ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል << Do this in remembrance of me >> የሉቃስ ወንጌል 22 ፥ 19 ፤ 1 ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 24 _ 25 ይህ ለመኖርያችን ዋጋ ለመክፈል በአዕምሮ ወይም በሥጋ የምንጨነቅበት ሳይሆን ግሩምና ድንቅ የሆነውን የጌታን የማዳን ሕይወትና አገልግሎት ለማስታወስ ነው ይህ የጌታ እራት ጥልቅ የሆነውን ምሥጋናና አድናቆት ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ስላደረገልን ለመግለጽ ትልቅ በዓል ወይንም በእንግሊዘኛው Occasion ነው በአይሁድ የፋሲካ እራት ጊዜ የዕብራውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ መውጣት የታወጀ አንድ ደረጃም ወደፊት የሄደ ነበረ በዘጸአት 12 ፥ 26 እና 27 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን እንዲህም ይሆናል፤ ልጆቻችሁ፦ ይህ አምልኮ ለእናንተ ምንድር ነው ? ባሉአችሁ ጊዜ፥ እናንተ፦ በግብፅ አገር በእስራኤል ...