Posts

Showing posts from June, 2015

የጌታ እራት ክፍል ሁለት

Image
የጌታ እራት ክፍል ሁለት የተወደዳችሁ ወገኖች ይህ ዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው ትምህርት የክፍል ሁለት ትምህርት ነው በክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ የጌታን እራት መውሰድ አስመልክቶ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች የጌታን እራት መውሰድ ሲለማመዱ 1 ኛ ቆሮንቶስ 10 ፥ 16 ላይ የተጻፈውን ቃል መነሻ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ ከማብራርያ ጋር ጠቅለል ያለ ሃሳብ ወስደን በሰፊው ተማምረናል የዛሬው የክፍል ሁለት ትምህርት ከዚሁ የቀጠለ ነው በዚህ ክፍለ ትምህርት የጌታን እራት የምንጠቀመው በ1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 20 መሠረት ነው የመልዕክቱ ክፍል እንዲህ ይላል እንግዲህ አብራችሁ ስትሰበሰቡ የምትበሉት የጌታ እራት አይደለም በመብላት ጊዜ እያንዳንዱ የራሱን እራት ይበላልና አንዱም ይራባል አንዱም ይሰክራል ይለናል ከዚህ ሃሳብ እንደምንረዳው እንግዲህ ሰው የጌታን እራት ለመውሰድ ይሰበሰባል ነገር ግን የተሰበሰበ ሁሉ ስለተሰበሰበ ብቻ የጌታን እራት መውሰድ የለበትም ይህንን ያልኩበት ትልቅ ምክንያት ስላለኝ ነው ብዙ መንፈሳውያን ነን የሚሉ ሰዎች በምን ጉዳይ ይሁን በምን አይታወቅም ስለተሰበሰቡና ስብሰባቸውም ስለተቃናላቸው ብቻ እንዲያው በሞቅታ ተነስተው የጌታን እራት በቤተክርስቲያን በቅዱሳን ኅብረት መካከል ሳይሆን በያሉበት መንደርና ቀዬ ሁሉ እንውሰድ ይላሉ በትክክልም ይወስዳሉ ማለትም   ተነስተው እነርሱ የጌታ እራት ነው ብለው ያሰቡትንና   የሰየሙትን   ለእነርሱም የጌታ እራት የሆነ...