በር መሠማርያ የሕይወት መገኛ የሚያድን ምግባችን ሃይማኖተ አበው እልመስጦግያ ምዕራፍ 3
ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ ትምህርት ነው ክፍል ሁለት ጥንተ አንቀጽ መካነ ሕይወት ፈውስነ ሲሳይነ ስቴነ መኮንንነ ትርጉም ፦ በር መሠማርያ የሕይወት መገኛ የሚያድን ምግባችን የሚፈርድልን መጠጣችን ነው ሃይማኖተ አበው እልመስጦግያ ምዕራፍ 3 ኢየሱስም ደግሞ አላቸው እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸው...