Posts

Showing posts from February, 2015

ስለእኛ ተሰቀለ በመስቀሉም ጽናችን ቤዛችን ድኅነታችን ተደረገልን ሃይማኖተ አበው

ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር የሚቀርብላችሁ ትምህርት ነው       ተሰቅለ በእንቲአነ ወበመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ ጽንዕነ ቤዛነ     ስለእኛ ተሰቀለ በመስቀሉም ጽናችን ቤዛችን ድኅነታችን ተደረገልን     ሃይማኖተ አበው     እልመስጦአግያ     ምዕራፍ አራት     ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ   1ኛ ጴጥሮስ 2 ፥ 24     የተወደዳችሁ ወገኖች ዛሬ የምንመለከተው እነዚህን በሃይማኖተ አበው የተጻፈውንና ጴጥሮስ በመልዕክቱ የጠቀሰልንን ሃሳቦች በማገናኘት ፣ በማዛመድም ነው ሁለቱም ሃሳቦች ማለት በጴጥሮስ መልዕክት የተጠቀሰውና በሃይማኖተ አበው የተጻፉት ሃሳቦች አንድ ዓይነት ናቸው ሁለቱም ሃሳቦች በደኅንነታችንና በፈውሳችን ዙርያ እርግጠኞች ሆነን ክርስቶስ ለጽድቃችን ፣ ለመዳናችን ፣ ለመጽናታችንም በመስቀል ላይ በሞቱ የሠራውን ሥራ በእምነት እንድንቀበል የሚያስታውሱንና የሚናገሩን ናቸው ሃይማኖተ አበው የተባለው መጽሐፍ ስለእኛ ተሰቀለ በመስቀሉም ጽናችን ቤዛችን ድኅነታችን ተደረገልን ሲል በእግዚአብሔር ቃል...